2009-10-19 13:32:10

የስነ ከዋክበት ዓመት


ባለፈው ሓሙስ በቫቲካን ቤተ መዘክሮች ጋሊለዮ ጋሊለይ የተወለደበት 400ኛው ዓመት ምክንያት የስነ ከዋክብት መገልጫ ትርኢት መቅረቡ ሲገለጥ፣ ይህ እ.ኤ.አ. እስከ ጥር 16 ቀን 2010 ዓ.ም. የሚቆየው ትርኢት በማስመልከት የቅድስት መንበር የዜና RealAudioMP3 እና የማኅተም ክፍል ኃላፊ የቫቲካን ረዲዮ አስተዳዳሪ ኣባ ፈደሪኮ ሎምባርዲ መግለጫ ሲሰጡ፣ መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ 8 “ጌታ እግዚአብሔር ሆይ ስምህ በዓለም ሁሉ የተመሰገነ ነው። ለአንተ የሚቀርበው ምስጋና ከሰማይ በላይ ከፍ ያለ ነው። … የፈጠርከው ሰማይ በማይበት ጊዜ፣ በየስፍራቸው አጽንተህ ያኖርሃቸውን ጨረቃን እና ከዋክበት በምመለከትበት ጊዜ… “ የሚለውን ጸሎት በመጥቀስ፣ በዚህ በ 2009 ዓ.ም. በመታሰብ ላይ ያለው የስነ ከዋክብት ዓመት ይኽንን የእግዚአብሔር ድንቅ ሥራ የሚስተነተንበ መሆኑ ገልጠው፣ የሰው ልጅ በተለያዩ እለታዊ ጉዳዮች ተከቦ እና ተዋክቦ ተፈጥሮን የማድነቅ ጥልቅ ስሜቱን ችላ እያለ ነው፣ ስለዚህ ይህ ዓመት የሰው ልጅ የእግዚአብሔር ድንቅ ሥራ የሆነው ተፈጥሮን እና አካባቢውን ዳግም በመመልከት እራሱን ወደ እግዚአብሔር ያቀና ዘንድ የሚያነቃቃበት ዓመት ነው ብለዋል።

የቫቲካን የስነ ከዋክብት ምርምር እና የጥናት ማእከል ይኸንን የስነ ከዋክብት ዓመት ምክንያት በማድረግ በእምነት እና በምርምርን መካከል ያለውን ግኑኝነት የሚያንጸባርቅ የተለያዩ የስነ ከዋክብት ትርኢቶች በቫቲካን ቤተ መዘክሮች እየቀረቡ ናቸው ብለዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.