2009-10-19 18:26:54

ዘመነ ጽጌ 2ኛ ከ(http://www.ethiocist.org/index.php?option=com_content&view=article&id=189&Itemid=27) የተወሰደ


የእግዚአብሔር ክብር - ለድምጹ ታማኝ መሆን የሰው ልጅ በሕይወቱ ለነገሮችም ሆነ ለሰው ማድረግ የሚገባውን ነገር ሲያደርግ ይበልጥ ደስታና የኅሊና ዕረፍት ይሰማዋል፤ በተቃራኒውም ማድረግ የሚገባውን ካላደረገ ውስጡ አያርፍም። ይህ እውነት ደግሞ ከፍ ባለ ደረጃ የሚጎላው በእግዚአብሔር ፊት ማድረግ ወይም መሆን የሚገባንን ካልሆንንና ካላደረግን ነው፤ ምክንያቱም ቋሚ ወይም ቀጣይ ጎዶሎነትን ስለምንሰንቅ ነው። ስለዚህም እግዚአብሔርን በሕይወታችን የማክበርና የማስከበር ነገር ማድረግ የሚገባን ነገር ነውና ይህን ካልተለማመድን ነገሮች ሁሉ ቢሆኑልን እንኳ የጎዶሎነት ስሜታችን ሁሌም እየጎደለ ነው የሚቀጥለው። እግዚአብሔርን ማክበር ሰው የመሆኔን ትርጉም የሚሰጠኝ ከሆነ ከዚህ ዓላማ የሚያስተጓጉለኝ ነገር ምንድነው ብለን ማሰብ ይኖርብናል። የዛሬው ወንጌል ለዚህ አጋዥ ነጥቦች አሉት። መጀመሪያው ቁጥር ላይ የዮሐንስ ደቀመዛሙርት የክርስቶስን ተከታይ ማግኘትና ማጥመቅ በማወቃቸው ዮሐንስ መጥምቁን ከኢየሱስ ጋር ማወዳደርና ምናልባትም የትኛው ነው ትክክለኛ በሚል ሃሳብ ውስጥ ሆነው <<መምህር ሆይ፥ በዮርዳኖስ ማዶ ከአንተ ጋር የነበረው አንተም የመሰከርህለት፥ እነሆ፥ እርሱ ያጠምቃል ሁሉም ወደ እርሱ ይመጣሉ>> አሉት። ይሄ መስመር ለኛ ብዙ ሊለን ይገባል። ምክንያቱም ብዙ ጊዜ እኛን የሚናገረንና ሰዎችም የሚከተሉት ኢይሱስ ብቻ ቢሆን ኖሮ የእሱ ተከታይነታችን ቀለል ባለ ነበር። እውነቱ ግን ከዚህም ከዚያም የሚናገሩን፣ ተስፋ እየሰጡን ተከተሉኝ በማለት ጊዜያችንንና ኃይላችንን እንድናባክንላቸው የሚጋብዙን የኑሮ ምርጫዎች ብዙ ናቸው። እውነተኛ ተፈጥሮዋቸው ግን ሁሌም አንድ ሆኖ ይቀራል፦ <<እኔ ክርስቶስ አይደለሁም>> (ቁ.28) ማለትም እነርሱ ክርስቶስ አይደሉም። የምንሮጥላቸው ማናቸውም ነገሮች እውነተኛ መልስ እነሱ ክርስቶስ ያለመሆናቸው ነው። እድሜያችንን፣ ገንዘባችንን፣ እውቀታችንን፣ ጉልበታችንን… በጣም ካባከንንላቸውና ካሟጠጡን በኋላ እህሳ ብለን ብንጠይቃቸው መጨረሻ ላይ የሚሉን ነገር <<እኔ ክርስቶስ አይደለሁም>>ነው። ምክንያቱም መሆን ስላልፈለጉ ሳይሆን መሆን ስለማይችሉ ማለት ነው። ስለዚህ እግዚአብሔርን በዕለታዊ ሩጫው ለማክበር የሚተጋ ክርስቲያን ከእንደዚህ ዓይነት የማንነት ኪሣራ ይድናል። ክርስትናችንን ባመንን መጠን ብቻ ሳይሆን በኖርነው መጠን ፍጻሜያችን እየተወሰነ ይሄዳል፤ <<እርሱ ሊልቅ እኔ ግን ላንስ ያስፈልጋል>>(ቁ.30) እንዳለው ዮሐንስ መጥምቅ እኛም ክርስቶስ ሊልቅ፣ ከፍ ሊል እኔ ወይም እገሊት ወይም የሆነ የምናስቀድመው ነገር ካለም ዝቅ ሊል ያስፈልጋል ማለትን መለማመድ አለብን። ይህ ሲሆን ቁ.36 ላይ <<በልጁ የሚያምን የዘላለም ሕይወት አለው፤ በልጁ የማያምን ግን የእግዚአብሔር ቍጣ በእርሱ ላይ ይኖራል እንጂ ሕይወትን አያይም>> እንደሚለው የጉዟችን ፍጻሜ ክርስቶስ ይሆናል። እምነታችም ፍላጎት ብቻ መሆኑ ቀርቶ ሕይወትና መዳንን ያጎናጽፈናል። ስለዚህ በሕይወታችን ለሚጠሩን ነገሮች ሁሉ መልስ መስጠት አንችልም። ብንችልም እንኳ የነሱ ምላሽ ጊዜያዊ ነው። በመላ ማንነታችን ቀጣይና ሙሉ ምላሽን ልናገኝ የምንችለው በልባችን ውስጥ ክርስቶስ እንዳይቀመጥ ቦታ ያጣበቡ ነገሮችን ለማስወገድ ስንታገል የእግዚአብሔርም ጸጋ በቃሉና በምሥጢራቱ ለዚህ ግብ እንደሚያግዘን ስናምን ገና መጨረሻ ላይ ሳይሆን በየዕለቱ ሰላማችንና ዕረፍታችን በችግር መሐል ቢሆንም እየበዛ ይሄዳል። እግዚአብሔር በብዙ መልኩ ይናገረናል፤ በእውነት እሱን በሕይወታችን ማክበር ጥማታችን ከሆነ ለድምጹ ታምኝ እንሁን። የቤተ ክርስቲያንም ጩኸት ከርሱ የተለየ ሌላ ድምጽ ሳይሆን የእርሱን ድምጽ ለዚህ ዘመን በሚሆን መልኩ የምታስተላልፍ የክርስቶስ አካል ናትና ወደ ማንም ሳይሆን ወደ ቃሉና ወደ ማዕደ ቁርባን የሚጠራንንን ድምጿን እናዳምጥ። ይህ ሲሆን በርግጥም ሌሎች ነገሮች ዝቅ ክርስቶስ ከፍ ሊል ይገባል የሚል ምስክርነትን ለዓለም መስጠት ጀመርን ማለት ነው። የእግዚአብሔር ክብር - ለድምጹ ታማኝ መሆን ኤፌ.5:21-33 ራእይ 21:1-8 ሐዋ. 21:31-40 ዮሐ,3:25-36 የሰው ልጅ በሕይወቱ ለነገሮችም ሆነ ለሰው ማድረግ የሚገባውን ነገር ሲያደርግ ይበልጥ ደስታና የኅሊና ዕረፍት ይሰማዋል፤ በተቃራኒውም ማድረግ የሚገባውን ካላደረገ ውስጡ አያርፍም። ይህ እውነት ደግሞ ከፍ ባለ ደረጃ የሚጎላው በእግዚአብሔር ፊት ማድረግ ወይም መሆን የሚገባንን ካልሆንንና ካላደረግን ነው፤ ምክንያቱም የትም እንግባ የት፣ እዚህም እንሁን እዚያ፣ ከእነገሌ ጋርም እንሁን ብቻችንን ቋሚ ወይም ቀጣይ ጎዶሎነትን ስለምንሰንቅ ነው። ስለዚህም እግዚአብሔርን በሕይወታችን የማክበርና የማስከበር ነገር ማድረግ የሚገባን ነገር ነውና ይህን ካልተለማመድን ነገሮች ሁሉ ቢሆኑልን እንኳ የጎዶሎነት ስሜታችን ሁሌም እየጎደለ ነው የሚቀጥለው። እግዚአብሔርን ማክበር ሰው የመሆኔን ትርጉም የሚሰጠኝ ከሆነ ከዚህ ዓላማ የሚያስተጓጉለኝ ነገር ምንድነው ብለን ማሰብ ይኖርብናል። የዛሬው ወንጌል ለዚህ አጋዥ ነጥቦች አሉት። መጀመሪያው ቁጥር ላይ የዮሐንስ ደቀመዛሙርት የክርስቶስን ተከታይ ማግኘትና ማጥመቅ በማወቃቸው ዮሐንስ መጥምቁን ከኢየሱስ ጋር ማወዳደርና ምናልባትም የትኛው ነው ትክክለኛ በሚል ሃሳብ ውስጥ ሆነው <<መምህር ሆይ፥ በዮርዳኖስ ማዶ ከአንተ ጋር የነበረው አንተም የመሰከርህለት፥ እነሆ፥ እርሱ ያጠምቃል ሁሉም ወደ እርሱ ይመጣሉ>> አሉት። ይሄ መስመር ለኛ ብዙ ሊለን ይገባል። ምክንያቱም ብዙ ጊዜ እኛን የሚናገረንና ሰዎችም የሚከተሉት ኢይሱስ ብቻ ቢሆን ኖሮ የእሱ ተከታይነታችን ቀለል ባለ ነበር። እውነቱ ግን ከዚህም ከዚያም የሚናገሩን፣ ተስፋ እየሰጡን ተከተሉኝ በማለት ጊዜያችንንና ኃይላችንን እንድናባክንላቸው የሚጋብዙን የኑሮ ምርጫዎች ብዙ ናቸው። እውነተኛ ተፈጥሮዋቸው ግን ሁሌም አንድ ሆኖ ይቀራል፦ <<እኔ ክርስቶስ አይደለሁም>> (ቁ.28) ማለትም እነርሱ ክርስቶስ አይደሉም። የምንሮጥላቸው ማናቸውም ነገሮች እውነተኛ መልስ እነሱ ክርስቶስ ያለመሆናቸው ነው። እድሜያችንን፣ ገንዘባችንን፣ እውቀታችንን፣ ጉልበታችንን… በጣም ካባከንንላቸውና ካሟጠጡን በኋላ እህሳ ብለን ብንጠይቃቸው መጨረሻ ላይ የሚሉን ነገር <<እኔ ክርስቶስ አይደለሁም>>ነው። ምክንያቱም መሆን ስላልፈለጉ ሳይሆን መሆን ስለማይችሉ ማለት ነው። ስለዚህ እግዚአብሔርን በዕለታዊ ሩጫው ለማክበር የሚተጋ ክርስቲያን ከእንደዚህ ዓይነት የማንነት ኪሣራ ይድናል። ክርስትናችንን ባመንን መጠን ብቻ ሳይሆን በኖርነው መጠን ፍጻሜያችን እየተወሰነ ይሄዳል፤ <<እርሱ ሊልቅ እኔ ግን ላንስ ያስፈልጋል>>(ቁ.30) እንዳለው ዮሐንስ መጥምቅ እኛም ክርስቶስ ሊልቅ፣ ከፍ ሊል እኔ ወይም እገሊት ወይም የሆነ የምናስቀድመው ነገር ካለም ዝቅ ሊል ያስፈልጋል ማለትን መለማመድ አለብን። ይህ ሲሆን ቁ.36 ላይ <<በልጁ የሚያምን የዘላለም ሕይወት አለው፤ በልጁ የማያምን ግን የእግዚአብሔር ቍጣ በእርሱ ላይ ይኖራል እንጂ ሕይወትን አያይም>> እንደሚለው የጉዟችን ፍጻሜ ክርስቶስ ይሆናል። እምነታችም ፍላጎት ብቻ መሆኑ ቀርቶ ሕይወትና መዳንን ያጎናጽፈናል። ስለዚህ በሕይወታችን ለሚጠሩን ነገሮች ሁሉ መልስ መስጠት አንችልም። ብንችልም እንኳ የነሱ ምላሽ ጊዜያዊ ነው። በመላ ማንነታችን ቀጣይና ሙሉ ምላሽን ልናገኝ የምንችለው በልባችን ውስጥ ክርስቶስ እንዳይቀመጥ ቦታ ያጣበቡ ነገሮችን ለማስወገድ ስንታገል የእግዚአብሔርም ጸጋ በቃሉና በምሥጢራቱ ለዚህ ግብ እንደሚያግዘን ስናምን ገና መጨረሻ ላይ ሳይሆን በየዕለቱ ሰላማችንና ዕረፍታችን በችግር መሐል ቢሆንም እየበዛ ይሄዳል። እግዚአብሔር በብዙ መልኩ ይናገረናል፤ በእውነት እሱን በሕይወታችን ማክበር ጥማታችን ከሆነ ለድምጹ ታምኝ እንሁን። የቤተ ክርስቲያንም ጩኸት ከርሱ የተለየ ሌላ ድምጽ ሳይሆን የእርሱን ድምጽ ለዚህ ዘመን በሚሆን መልኩ የምታስተላልፍ የክርስቶስ አካል ናትና ወደ ማንም ሳይሆን ወደ ቃሉና ወደ ማዕደ ቁርባን የሚጠራንንን ድምጿን እናዳምጥ። ይህ ሲሆን በርግጥም ሌሎች ነገሮች ዝቅ ክርስቶስ ከፍ ሊል ይገባል የሚል ምስክርነትን ለዓለም መስጠት ጀመርን ማለት ነው።







All the contents on this site are copyrighted ©.