2009-10-19 13:29:21

እዚህ በቫቲካን በመካሄድ ላይ ያለው የአፍሪቃው ሲኖዶስ ለአፍሪቃ ተሃድሶ ጥሪ ነው


እ.ኤ.አ. በ 1994 ዓ.ም. ከተካሄደው አንደኛው የአፍሪቅ ብፁዓን ጳጳሳት ሲኖዶስ ቀጥሎ ልክ በ 15ኛው ዓመቱ በመካሄድ ላይ ያለው ሁለተኛው ሲኖዶስ ባለፉት 15 ዓመታት በአፍሪቃ የታዩት ለውጦች የካቶሊክ ቤተ ክርስትያን እድገት ማኅበራዊ ፖለቲካዊ እና ኤኮኖሚያዊ ብሎም ሰብአዊ ለውጦች እግምት ውስጥ በማስገባት የሚገመግም እና አዲስ የሂደት መመሪያ የሚያቀርብ መሆኑ RealAudioMP3 የታንዛኒያ የሶንገአ ሊቀ ጳጳሳት ብጹዕ ኣቡነ ኖርበርት ምተጋ ከቫቲካን ሬዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ አሳሰበው፣ የአፍሪቃ ህዝብ በቤተ ክርስትያን እና በአገሩ ጉዳይ ንቁ ተሳታፊ ይሆን ዘንድ እያሳሰበ ያለው ሁለተኛው የአፍሪቃ ብፁዓን ጳጳሳት ሲኖዶስ፣ የሰው ልጅ የተሟላ እድገት፣ የሕጻናት እና የሴቶች መብት እና ፈቃድ ጥበቃ በጠቅላላ የሕዝብ ህሊና የሚያነቃቃ እና የአፍሪቃ ካቶሊክ ምእመን በቤተ ክርስትያኑ በግንባር ቀደም እንዲሳተፍ እና ወንጌልን በእለታዊ ኑሮው እንዲመሰክር፣ በዚህ ዓይነት ሕይወት በቤተ ክርስትያን ሓዋርያዊ ግበረ ተልእኮ ተሳታፊ መሆኑ ለማሳሰብ ተገቢ መሆኑ የሲኖዶስ ብፁዓን አበው አስገንዝበዋል ሲሉ። በአንጎላ የሉባንጎ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ጋብሪየል ምቢሊንጊ የአፍሪቃው ማህበራዊ ህይወት የግለኝነት ማለትን እያንዳንዱ በተናጥል የሚኖረው የሕይወት ስብስብ ሳይሆን፣ በማኅበርሰብ የሚገለጥ ማኅበራዊነትን የሚያጎላ ነው፣ የተናጥል ሕይወት በጋራው ሕይወት ላይ የተገነባ መሆኑ በማብራራት፣ ስለዚህ የአፍሪቃው ባህል የቤተ ክርስትያናዊነት መገልጫ ነው ለማለት ይቻላል ካሉ በኋላ፣ ይህ ዓይነት ባህል ያለው ህዝብ ለእርቅ ለፍትህ እና ለሰላም ማነቃቃት ከተፈለገ ህዝቡ ላለው ባህል አቢይ ግምት ሊሰጠው ይገባል በማለት የሰጡትን ቃለ ምልልስ ደምድመዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.