2009-10-19 13:30:36

ሙዚቃ ጸሎት መሆን ይችላል


ባለፈው ቅዳሜ ለቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ እና እንዲሁም ለአፍሪቃ ሲኖዶስ ብፁዓን አበው ክብር ቫቲካን በሚገኘው በጳውሎስ 6ኛ የጉባኤ አዳራሽ በፒያኖ የሚዚቃ መሣሪያ አቀንቃኝ የቻይና ተወላጅ ጂን ጁ የተመራ RealAudioMP3 የሙዚቃ ትርኢት መቅረቡ ተገልጠዋል።

ቅዱስ ኣባታችን የሙዚቃው ትርኢት እንዳበቃ ባሰሙት ንግግር፣ የውበት የውህደት እና የመንፈስ ጥልቅ መግለጫ የሆነው ሙዚቃ አቢይ የጸሎት መሣሪያ መሆኑና ለእግዚአብሔር ክብር የሚቀርበው ሙዚቃ ጸሎት መሆኑ በማብራራትም፣ ይህ ታላላቅ የሙዚቃ አቀንቃኞች እና ደራሲዎች ያቀረቡት ጥናታዊው ሙዚቃ፣ አሁንም ህያው ሆኖ ትውልድ የሚሸኝ ፈጽሞ የማይሰለች መሆኑ ቅዱስ አባታችን በማብራራት፣ ሙዚቃ የዓለም ሕዝብ ቋንቋ ሁሉንም የሚያገናኝ ዓለም አቀፍ ጥልቅ ቋንቋ እና የሰው ልጅ ጥልቅ ስሜት መግለጫ መሆኑ ገልጠው፣ በቃላት ሊገለጥ የማይቻለውን ውበት በጣዕመ ልሳን እና የሙዚቃ መሣሪያ በማቀንቀን ከጥንት ጀምሮ ሲገለጥ መቆየቱ በማስታወሰ፣ ሙዚቃ የሰው ልጅ ትልቅ ሃብት ነው ብለዋል።

ሙዚቃ በሃዘንም በደስታ ይሁን መንፈስን ልብን እና አእምንሮን ወደ እግዚአብሔር እንዲያቀና የሚያግዝ የሰው ልጅ ውስጠ ሁኔታ የሚገልጥ ጥልቅ ቋንቋ ነው፣ በሌላው አገላለጥ ሙዚቃ ጸሎት ሊሆን እንደሚችል አስረድተዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.