2009-10-16 13:46:03

የአፍሪቃ ሲኖዶስ፣ አፍሪቃ የራሷ ዕጣ እድል ግንባር ቀደም ተወናያን


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲቶኮስ 16ኛ በተገኙበት እዚህ በቫቲካን እርቅ ፍትህ እና ሰላም በሚል ዋና ርእስ ተመርቶ በመካሄድ ላይ ያለው ሁለተኛው የአፍሪቃ ብፁዓን ጳጳሳት ሲኖዶስ ትላትና ባካሄደው 15ኛው የስብሰባው ቀን የሲኖዶስ የማጠቃለያ RealAudioMP3 ሰነድ ፈር የሚያስዝ መሆኑ የሚነገርለት የሲኖዶስ ብጹዓን አበው በቡድን ተከፋፍለው የዳሰሱዋቸው ርእሶች እና የተሰጡት አስተያየቶች፣ ተጠናቅሮ የቀረበውን ሰነድ በማስደገፍ ውይይት መካሄዱ ተገልጠዋል።

አፍሪቃ ትቀድም ዘንድ የራሷ ዕጣ ዕድል ባለ ቤት እና የዚህ ዕጣ ዕድል ግንባር ቀደም ተወናያን ትሆን ዘንድ ብፁዓን ጳጳሳት በማሳሰብ፣ የገዛ እራስዋ ክብር ግንዛቤ እንዲኖራት ብሎም የትንሳኤ ተስፋ የተላበሰች፣ የሥራ እና የበረታ ማኅበርሰብአዊ ጉባኤ መሆኗ ብፁዓን ጳጳሳቱ አሳስበዋል። የሲኖዶስ ብፁዓን አበው በተናንሽ ቡድኖች ተከፋፍለው ባካሄዱት ውይይት በዚህች ክፍለ ዓለም የተከናወኑት እና ቤተ ክርስትያን ያከናወነቻቸው ሥራዎች መለስ ብለው በመቃኘት፣ ክንዋኔዎቹ አወንታዊ መሆናቸው በመግለጥ፣ የተፈጥሮ አካባቢን መንከባከብ ጥሪዎችን ለይቶ በማወቅ ከክርስትናው ባህል ጋር የሚጣጣሙት፣ በሚፈጸም ጥፋት የመታመን እና ስሕተትን ላለ መድገም ቁርጥ ፍቃድ የማድረግ ሥርዓት የተላበሱት የአፍሪቃ ባህሎች፣ በአፍሪቃ ለማረጋገጥ የታለመው እርቅ እግብ ለማድረስ እና የዚህ ሂደቱ መሠረት እንደሆኑ ማሰብ ወሳኝ መሆኑ አሥምረውበታል።

ስለዚህ የሲኖዶስ ብፁዓን አበው የቤተ ክርስትያን የማኅበራዊ ትምህርት በአፍሪቃ በሚገባ እንዲስፋፋ በተለይ ደግሞ ስለ ጾታዊ ስሜት የሚመለከተው ትምህርት፣ ስለ ሠራተኞች ስለ ቤተሰብ ስለ ሴቶች ጉዳይ የሚከታተል እና የሚንከባከብ ሓዋርያዊ ግብረ ኖልዎ መኖር እንዳለበት በማስገንዘብ፣ የአፍሪቃን ህዝብ ላደጋ የሚያጋልጠው የጥንቆላ እና የመተት ተግባሮች እንዲወገዱ እና እንደየ አገሩ የሚለያየው የምስልምናው ሃይማኖት እግምት ውስጥ በማስገባት ከምስልምናው ሃይማኖት ጋር የሚደረገው ውይይት በሚገባ እና ጠለቅ አድርጎ ማጤን ተገቢ መሆኑ ብፁዓን አበው አሳስበዋል።

ለቤተ ክርስትያን ግኑኝነቶች እና ቤተ ክርስትያን ለማህበራዊ እና ለሰብአዊ ሕንጸት የምትሰጠው አስተምህሮ ለሁሉም ለማዳረስ፣ የመገናኛ ብዙኃን እጅግ አስፈላጊ መሆናቸው ብፁዓን ጳጳሳት በማሳሰብ፣ የቴሌቭዥን እና የሬድዮ ጣቢያዎች በአፍሪቃ የቤተ ሰብ መሠረት የሆነውን ጤናማው ባህል እና እሴቶችን ለማስተጋባት የሚያገለግሉ የእውነት መሣሪያዎች መሆን እንድሚገባቸው በመጥቀስ፣ አፍሪቃ እጅግ እያሰቃየ ያለው ፖለቲካዊ ቀውስ ለመቅረፍ፣ የእርቅ ሂደት ወሳኝ መሆኑ እና የዚህ ክፍለ ዓለም ቤተ ክርስትያን በመንግሥት እና በፖለቲካው መድረክ በሚከሰተው ውጥረት እና ግጭት ለአንዱ ወገን ሳታደላ እና የዚህ ችግር ታጋች ሳትሆን፣ መሪዎች በሚገባ የተቀበሉትን ኃላፊነት አለ አድልዎ አለ ሙስና እንዲወጡ በሐሳብ እና በጸሎት አስተይየት በመስጠትም ጭምር እንደምትሸኛቸው የሲኖዶስ አበው በማሳሰብ፣ የአፍሪቃ ቤተ ክርስትያን ማኅበራዊ ፖለቲካዊ እና ኤኮኖሚው ጉዳይ በተመለከተ በቤተ ክስትያን ማኅበራዊ ትምህርት የተሸኘ ንቁ ተሳትፎ ሊኖራ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

ብፁዓን አፍሪቃውያን ጳጳሳት በቡድን ተከፋፍለው ባካሄዱት የክብ ጠረጴዛ ውይይት፣ የጦር መሣሪያ ሕገ ወጥ ዝውውር እና እሽቅድድም፣ የአደንዛዥ እጸዋት መስፋፋት፣ የሴቶች ግርዛት፣ ቀዛፊው ተዛማቹ የኤይድስ በሽታ የመሳሰሉት፣ አፍሪቃን አንቀው ወደ ኋላ የሚያስቀሩዋት ሁሉ አንድ በአንድ በመገንዘብ፣ መፍትሔ እንዲያገኙ የምትከተለው መንገድ በመመርመር አዲስ የሕይወት ጎዳና እንድትከተል ጥሪ በማቅረብ፣ የካቶሊክ መናብረተ ጥበብ እና ትምህርት ቤቶች በመደገፍ፣ የዘርአ ክህነት ትምህርት ቤቶች ብቻ ሳይሆኑ፣ ዓለማውያን ምእመናን ጭምር ያሚሳተፉበት እንዲሆኑ ማበረታታት አስፈላጊ መሆኑ የገለጡት ብፁዓን ጳጳሳት፣ የአፍሪቃ ቤተ ክርስትያን ዓለማውያን ምእመናን ለአስፍሆተ ወንጌል አቢይ እስተዋጽኦ የሚሰጡ መሆናቸው መረዳት ይኖርባታል እንጂ የዓለማውያን ምእመናን ሥጋት ሊኖራት ኣይገባም ብለዋል።

በመጨረሻ ብፁዓን አበው አፍሪቃዊ የቅዱስ ቁርባን ጉባኤ እንዲቋቋም እና ስለ የአፍሪቃ ሴቶች ጉዳይ የሚወያይ አፍሪቃ አቀፍ ስብሰባ እንዲጠራ እና የተለያዩ ሃይማኖቶችን የሚያገናኝ የጋራ የጸሎት መርሃ ግብር ቀጣይነት ባለው ሂደት እንዲወጠን ሀሳብ ማቅረባቸውም ከሲኖዶስ አዳራሽ የተላለፈልን ዜና ያመለክታል።







All the contents on this site are copyrighted ©.