2009-10-14 13:19:23

የአፍሪቃ ብፁዓን ጳጳሳት ሁለተኛው ሲኖዶስ ትላትና የዳሰሳቸው ርእሶች

 


በቫቲካን በመካሄድ ላይ ያለው ይፋዊው የአፍሪቃ ብፁዓን ጳጳሳት ሁለተኛው ሲኖዶስ ትላንትና ባካሄደው 13ኛው የስብሰባው ቀን፣ ለአፍሪቃ ልማት መሠረት በዚህች ክፍለ ዓለም ያለው የጤና ጥበቃው ጉዳይ በበለጠ ማሻሻል ወሳኝ መሆኑ እንዳሠመረበት የሲኖዶስ መግለጫ ያመለክታል። ይህ እርቅ ፍትህ እና ሰላም በሚል ጠቅላይ ርእስ ሥር RealAudioMP3 ተመርቶ በመካሄድ ላይ ያለው የአፍሪቃ ብፁዓን ጳጳሳት ሲኖዶስ፣ ስለ ጤና ጥበቃ ጉዳይ በመወያየት ለየት ባለ መልኩ ስለ ቀዛፊው የኤይድስ በሽታ እና አፍሪቃን አንቆ እያሰቃየ ያለው በሕገ ወጥ አሠራር የሚከናወነው የመድሃኒት ንግድ በተመለከቱ ጉዳዮች በመወያየት፣ የሕይወት እሴቶች ለአደጋ እያጋለጠ ያለው የስነ ወሊድ ጤንነት በሚል ምክንያት የሚነዛው ጸረ ህይወት ባህል የሚያረማምደው ፖለቲካ ዙሪያ በመወያየት፣ የሕይወት እሴቶች ይከበሩ ዘንድ አሳስበዋል።

ሕይወት ከመጸነስ እስከ ባህርያዊ ሞት ክቡር እና ቅዱስ ነው፣ ቤተ ክርስትያን ይኸንን ባህል ለመከላከል እና ለማስፋፋትም ኃላፊነት እንዳላት የሲኖዶስ አበው በመግለጥ፣ አፍሪቃን እያሰቃየ ያለው የኤይድስ የወባ እና የቲቢ በሽታዎች ጉዳይ በመወያየት፣ የዚህ ክፍለ ዓለም ሕዝብ የጤና ጥበቃ መብት እንዲከበር እና የስነ ሕይወት ጥያቄዎች በተመለከተው ጉዳይ አቢይ አገልግሎት የሚሰጥ ልዩ ግብረ ኖልዎ ገቢራዊ ይሆን ዘንድ በማሳሰብ፣ የተለያዩ ተዛማች በሽታዎችን ለመግታት በሚደረገው ጥረት፣ ሁሉም ሃይማኖቶች በመተባበር እንዲሳተፉ ብጹዓን ጳጳሳት ጥሪ አቅርበዋል።

በአፍሪቃ የሚፈጸሙት ጽንስ የማስወረዱ ተግባር፣ የአምንዝራነት ሕይወት ምርጫ መሥፋፋት፣ ሁሉም ያው ነው በሚለው የዘመኑ ባህል እያስተግባው ባለው አመለካከት መሠረት እየተስፋፋ ያለው የጾታዊ ስሜት መዛባት እና ይኸንን የጾታዊ ስሜት መዛባት ለመፈወስ ይችላሉ የሚባሉት ገና በሙከራ ላይ ያሉ መድሃኒቶች ፍቱንነታቸውን ለመለየት በአፍሪቃ በሰው ላይ የሚደረገው ሙከራው ኢሰብአዊ ተግባር እና ይህ ድርጊት እያስከተለው ያለው የጤና መታወክ ብሎም የተለያዩ ችግሮች እያስከተለ መሆኑ ብጹዓን ጳጳሳት በመግለጥ ይህ ብዙ የማይነገርለት ጸረ ሰው ተግባር መሆኑ ብፁዓን ጳጳሳት በመግለጥ፣ አፍሪቃ ለሚፈለሰፉት መድሃኒቶች የሙከራ ምድር መሆን የለባትም ብለዋል።

ሌላው አፍሪቃን እያሰቃየ ያለው በኡጋንዳ ከ 20 እስከ 30 የሚገመቱት ሕጻናትን የሚመለከተው እርሱም ገና ለአቅመ አዳም ያልደረሱ ሕጻናት በወትድርናው ዓለም በማስገባት የሚፈጸመው ኢሰብአዊ ተግባር፣ ብፁዓን ጳጳሳቱ አውግዘው፣ በውትድርናው ዓለም የሚበዘበዙት የሕጻናት ብዛት እና በተለያዩ ጦርነቶች ለሞት የተዳርረጉት ሕጻናት ብዛት በውኑ የማይታወቅ ጉዳይ መሆኑ ብፁዓን ጳጳሳት በማሥመር፣ ይኸንን አፍሪቃን እያሰቃየ ያለው ችግር እንዲወገድ ቤተ ክርስትያን በወንጌልን ላይ የተመሠረተ የስነ ምግባር ባህል ማስፋፋት ግዴታ እንዳለባት የሲኖዶስ ብፁዓን አበው አሳስበዋል።

የአፍሪቃ ወጣት የኅብረተ ሰብ በተለያዩ በአፍሪቃ አገሮች በሚገኙት አቢያተ ክርስትያን በሚካሄደው የወጣቶች ቀን የሚያሳዩት ተሳትፎ የሚደነቅ መሆኑ እና በዚሁ ሱታፌ ወጣቱ ከመልክዓ ምድራዊ ጎሳዊ ብሎም ሃይማኖታዊ አጥር ባሻገር የእርቅ ባህል እግብር ላይ ለማዋል እንደሚቻል በመመስከር ላይ መሆኑ ከተገለጠ በኋላ፣ የአፍሪቃ ካቶሊክ ቤተ ክርስትያን ከምስልምናው ሃይማኖት ጋር የምታካሂደው ውይይት ሁሉም በአንድ አምላክ የሚያምኑ ሃይማኖትች እግዚአብሔር ፍቅር መሆኑ የሚያምኑ በመሆናቸውም ምክንያት፣ በዚህ ፍቅር ላይ የተመሠረተ ውይይት መሆኑ እና ይህ መለኮታዊ ፍቅር መግለጫ የሆነው ተጨባጭ ተግባር፣ የሁሉም ሃይማኖቶች ነጻነት ይከበር ዘንድ የሚያመለክት መሆኑም የሲኖዶስ ብፁዓን አበው በመግለጥ፣ በመጨረሻም በአፍሪቃ ዓለም አቀፍ ኅብረ ኢንዳስትሪዎች የሚፈጸሙት ዘርፈ ብዙ ብዝበዛ ማእከል በማድረግ በተፈጥሮ ሃብት የታደለቸው አፍሪቃ የዚህ ሃብት ተጠቃሚነቷ በተለያዩ ምክንያቶች በዓለም አቀፍ ኅብረ ኢንዳስትሪዎች ተረግጦ እንደሚገኝ እና ይህ የተፈጥሮ ሃብት ለልማት ከመሆኑ ይልቅ ለርስ በርስ ግጭት ለውጥረት እና ለሁከት ምክንያት እየሆነ መምጣቱንም በመጥቀስ፣ የሚከሰቱት ውጥረቶች ለሕገ ወጥ የጦር መሣሪያ ዝውውር አመች በመሆናቸውም ምክንያት፣ በአፍሪቃ ክልል የጦር መሣሪያ ባለ ቤትነት እያስፋፋ መሆኑ እና የተፈጥሮ ሃብት ለልማት እና ብልጽግና እንጂ ለግጭት እና ለብዝበዛ መሠረት መሆን የለበትም ብለዋል። በመጨረሻም በዚህች ክፍለ ዓለም የሚገኙት የቻይና ዜጎች ጉዳይ በመጥቀስም ለነዚህ በአፍሪቃ የሚገኙት የውጭ አገር ሠራተኞች ያቀና ሓዋርያዊ ግብረ ኖልዎ ማጠናከርም አስፈላጊ መሆኑ የሲኖዶስ ብፁዓን አበው በማሳወቅ የአፍሪቃ ክልል አቢያተ ክርስትያን ከምዕራቡ ዓለም አቢያተ ክርስትያን ጥገኝነት ይላቀቁ ዘንድ እና ይኸንን ጥሪ እግብር ላይ ለማዋል የሚያግዙ መንገዶች እንደተመለከተም ከሲኖዶስ አዳራሽ የተሰራጨው ዜና ያረጋግጣል።







All the contents on this site are copyrighted ©.