2009-10-14 13:25:54

በአፍሪቃ ብጹዓን ጳጳሳት ሁለተኛው ሲኖዶስ፣ የተባበሩት መንግሥታት የምግብ እና የእርሻ ድርጅት ዋና አስተዳዳሪ ያሰሙት ንግግር


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16 በተገኙበት እዚህ በቫቲካን በመካሄድ ላይ ባለው የአፍሪቃ ብፁዓን ጳጳሳት ሁለተኛው ሲኖዶስ ትላትና ከሰዓት በኋላ ባካሄደው ስብሰባ፣ የተባበሩት መንግሥታት የምግብ እና የርእሻ ድርጅት ዋና አስተዳዳሪ RealAudioMP3 ዣክ ዲዩፍ ንግግር ማሰማታቸው ተገለጠ።

የሰው ልጅ ምግብ የማግኘት መብት መከበር ያለበት መሠረታዊ ፍላጎት ነው፣ ከዚህ መሠረታዊው ፍላጎት ጋር ተያይዞ የሚሄዱ ትምህርት የማግኘት የጤና እንክብካቤ የመሳሰሉትን ማረጋገጥ ወሳኝ መሆኑ አመልክተው፣ ዘላቂነት ያለው የኤኮኖሚ እድገት ማረጋገጥ ለአፍሪቃ ሙሉአዊ እድገት ወሳኝ ነው ያሉት የተባበሩት መንግሥታት የምግብ እና እርሻ ድርጅት ዋና አስተዳዳሪ ዣክ ዲዩፍ በመቀጠልም፣ የአፍሪቃ የተፈጥሮ ሃብት የአፍሪቃ የኤኮኖሚ ነጻነት ማረጋገጫ መሆን እንዳለበትም በማብራራት፣ በአለማችን ተከስቶ ያለው የኤኮኖሚ ቀውስ በአፍሪቃ የነበረው ድኽነት ከፍ እንዲል ማድረጉንም ገልጠው፣ ባለፈው ዓመት በተመጣጠነ የምግብ እጥረት ይሰቃይ በነበረው የአፍሪቃ ህዝብ ብዛት ከፍ እንዲል እድርገዋል ካሉ በኋላ፣ በመቀጠልም ይኸንን ችግር ለመቅረፍ ምን መደረግ አለበት የሚለውን ጥያቄ በማንሳት፣ የአፍሪቃ የጤና ጥበቃ የትምህርት የኤኮኖሚው የማህበራዊው የሰብአዊው የአፍሪቃ አገሮች የንግድ ልውውጥ ሂደት ማሠልጠን የፖሊቲካው መዋቅር ማደስ ላነሱት ጥያቄ ተቀዳሚ መልስ መሆኑ አመልክተዋል።

በመጨረሻም በካሜሩን በኢትዮጵያን እና በጋናን እርሃብ ጨርሶ ለማስወገድ በመከናወን ላይ ያሉት የጸረ እርሃብ መርሃ ግብሮችን እንደ አብነት በመጥቀስ ከእርሃብ ነጻ የሆነ ዓለም ለማቆም የሚቻል ነው ካሉ በኋላ፣ በኢንዳስትሪ የበለጸጉት አገሮች የዓለም ሕዝብ የምግብ ዋስትና ለማረጋገጥ ለሚደገው ጥረት ድጋፍ የሚውል 21 ሚሊያርድ ዶላር መመደባቸውንም በማስታወስ እነዚህ በኢንዳስትሪ የበለጸጉት አገሮች ያሳዩት መልካም ፈቃድ የሚመሰገን ነው ብለዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.