2009-10-12 13:48:52

ብፁዕ አቡነ ብርሃነኢየሱስ ደምረው ሱራፍኤል፣ በአፍሪቃ የእንተ ላእለ ኵሉ ቤተ ክርስያን ማህበራዊ ትምህርት ማስፋፋት


እዚህ በቫቲካን የአፍሪቃ ብፁዓን ጳጳሳት ይፋዊው ሁለተኛው ሲኖዶስ እ.ፈ.አ. ከጥቅምት 4 ቀን 2009 ዓ.ም. ጀምሮ እየተካሄደ መሆኑ የሚታወስ ሲሆን፣ ይህ ሲኖዶስ ባለፈው ቅዳሜ የአዲስ አበባ ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ አቡነ በርሃነኢየሱስ ደምረው ሱራፍኤል ንግግር በማዳመጥ የመጀመሪያ ሳምንት ጉባኤው ማገባደዱ RealAudioMP3 ተገልጠዋል።

ብፁዕ አቡነ ብርሃነኢየሱስ ደምረው ሱራፊኤል በአፍሪቃ ኅበረት አንድ የቅድስት መንበር ቋሚ ታዛቢ አካል ይኖር ዘንድ ሀሳብ ማቅረባቸው እና ይህ ደግሞ ካቶሊክ ቤተ ክርስትያን ያላት ኵላዊነት ባህይርዋ እግምት ውስጥ ያስገባ መሆኑ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ በማብራራት፣ ቅድስት መንበር ስለ አፍሪቃ ጉዳይ ያላት አመለካከት ተሰሚነቱ እንዲጎላ በዚህ ኅብረት ዘንድ ሓዋርያዊ ወኪል ሊኖራት ያስፈልጋል። ይህ ያቀረቡት ሀሳብ የእስላም ሃይማኖት አብላጫ በሆኑባቸው የአፍሪቃ አገሮች ዘንድ ተቀባይነት ሊኖረው ይችልላ ወይ ለሚለው ለቀረበላቸው ጥያቄ ሲመልሱም፣ የካቶሊክ ቤተ ክርስትያን የምትደግፋቸው እና በህንጸት ረገድ የምታሰራጨው የሕይወት ባህል ሙሉ በሙሉ በሁሉም ሃይማኖቶች ተቀባይነት ያለው መሆኑ ገልጠው፣ የአፍሪቃ ኅብረት አባላት ከግማሽ በላይ የካቶሊክ እምነት ተከታይ መሆናቸውም አስታውሰው ስለዚህ እነዚህ የካቶሊክ እምነት ተከታይ አባላት ስለ የቤተ ክርስትያን የማኅበራዊ ትምህርት ጉዳይ በበለጠ እንዲረዱና እንዲያስተጋቡት የሚያግዝ ነው ብለው፣ ከዚህ አንጻር ስንመለከት ይላሉ ብፁዕነታቸው፣ ተቀባይነት የማያገኝ ሀሳብ ነው ለማለት አይቻልም ብለዋል።

ለሲኖዶስ ባሰሙት ንግግር ስለ ስደተኞች እና ተፈናቃዮች ጉዳይ መፍትሔ ለመሻት ከተፈለገ ሰዎች ከቦታ ቦታ እንዲዘዋወሩ የሚያስገድደው ዋነኛው ምክንያት ተለይቶ መፍትሔ ማግኘት ይኖርባታል ብለው፣ በተለይ ደግሞ ሴቶችን እና ከእድሜ በታች የሆኑትን ለከፋው አደጋ የሚያጋልጠው ሰዎችን የመሸጥ እና የመለወጥ አደገኛው ተግባር በተመለከተ የአፍሪቃ ቤተ ክርስትያን ቆራጥ ውሳኔ ማሰማት ይኖርባታል ብለዋል።

ብዙ የአፍሪቃ ህዝቦች ከአገሮቻቸው በሕግ ወጥተው በተለያዩ የኤውሮጳ አገሮች ለተለያዩ ሰብአዊው ክብር ላደጋ ለሚያጋልጥ የአደገኛ ተግባር መሣሪያ ሆነው ይገኛሉ፣ ይኽንን ሁሉ የሚያዘጋጅ የወንጀለኞች ቡድን እንዳለ የሚያመለክት ነው፣ ስለዚህ ከጦር መሣሪያ ዝውውር እና ከአደንዛዥ እጸዋት መስፋፋት ቀጥሎ ለሰዎች አደገኛ ሆኖ ያለው ችግር፣ ሰዎችን ከቦታ ቦታ የማዘዋወሩ ጉዳይ መሆኑ እና በዓለም አቀፍ ደረጃ ሕገ ወጥ ገበያ መሆኑም አብራርተው፣ በመጨረሻም ብዙ የኢትዮጳያ ዜጎች ወደ መካከለኛው ምሥራቅ ሥራ ፍለጋ እንደሚሰደዱ አስታውሰው፣ ይህ ወደ መከከለኛው ምሥራቅ መሰደድ ብዙ ኢትዮጵያውያን ክርስትያናዊ ባህላቸውን እና እምነታቸው እንዲክዱ እያስገደደ መሆኑ ገልጠው፣ ዜጎቻችን ተሰደው የሚጠመዱበት ሥራ እምብዛም ሙያ የሚጠይቅ አይደለም፣ ስለዚህ የአፍሪቃ ዜጎች ከዚህ የስደት አደጋ ለማዳን በገዛ አገራቸው በተለያዩ የሙያ ዘርፍ እንዲሰልጥኑ መደገፍ ያስፈልጋል ብለው፣ መፍትሔው ሕንጸት ማስፋፋት ነው ብለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.