2009-10-12 13:35:25

ቅዱስ አባታችን ነገሥታት ቤልጂም እና የፈረንሳይ ጠቅላይ ሚኒ. ተቀብለው አነጋገሩ


ባለፈው ቅዳሜ ጧት ቅዱስ አብታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ የበልጂም ንጉሥ አልበር ሁለተኛ እና ንግሥት ፓውላን ተቀብለው ካነጋገሩ በኋላ በመቀጠልም፣ ከፈረሳይ ጠቅላይ ሚኒ. ፍራምሶይስ RealAudioMP3 ፊሎን ጋር ተገናኝተዋል።

የርእሰ ሊቃ ጳጳሳት እና የቤልጂም ንጉስ ግኑኝነት የዓለም አቀፍ ፖለቲካዊ ጉዳዮች የአፍሪቃ የሰብአዊ መብት እና ፈቃድ ጥበቃ እንዲሁም የሕዝቦች እድገት የተሰኙት ርእሶችን የዳሰሰ እንደነበርም የቅድስት መንበር መገልጫ ያመልክታል።

ቅዱስ አባታችን ቀጥለው ከፈረንሳይ ጠቅላይ ሚኒ. ፍራንሶይስ ፊሎንን ጋር በመገናኘት ቅዱሱንታቸው በቅርቡ በፈረንሳይ እና በሉርድ ያካሄዱት ሓዋርያዊ ጉብኝት አስታውሰው፣ የፈረንሳይ እና የቅድስት መንበር የጋራ ግኑኝነቶች አክለውም የመካከለኛው ምስራቅ እና እዚህ በቫቲካን በመካሄድ ላይ ካለው የአፍሪቃ ብፁዓን ጳጳሳት ሁለተኛው ሲኖዶስ ጋር በማያያዝ ስለ የአንዳንድ የአፍሪቃ አገሮች ጉዳይ መወያየታቸው ከቅድስት መንበር የተሰራጨው መገልጫ ይጠቁማል።

በተካሄዱት ሁለቱ ግኑኝነቶች ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ፍቅር በሐቅ በሚል ርእስ ሥር የደረስዋት አዋዲት መልእክት በዓለማችን ተከስቶ ካለው የኤኮኖሚ መቃወስ ጉዳይ ጋር በማያያዝ አዋዲት መልእክቷ የምታመለክተው የመፍትሔ ሐሳቦች እና በተለይ ደግሞ ለተስተካከለው የኤኮኖሚ ሂደት ምን መደረግ እንዳለበት በአዋዲት መልእክቷ ዘንድ ቅዱስ አብታችን ያመለከቱት ሀሳብ እና በተከሰተው የኤኮኖሚ መቃወስ ምክንያት የድሆች አገሮች ኤኮኖሚ በበለጠ የተጎዳ መሆኑ እና ይኸንን ችግር ለመፍታትም ያሠፈሩት መመዘኛ ማእክል በማድረግ ጭምር ውይይት መካሄዱ እና አዋዲት መልእክቷ በዓለም አቀፍ ደረጃ ያላት ተሰሚነት አቢይ መሆኑ የመሰከረ ይፋዊ ግኑኝነት እንደነበር የቅዱስ መንበር የዜና እና የማኅተም ክፍል ያሰራጨው መገልጫ ይጠቁማል።








All the contents on this site are copyrighted ©.