2009-10-09 13:28:38

የአፍሪቃ ዘርፈ ብዙ ችግሮች እና ተስፋዎች፣ ከምዕራብ ዓለም ጋር ያላት ግኑኝነት


እርቅ ፍትሕ እና ሰላም በሚል ጠቅላይ ርእስ ሥር ተደግፎ እዚህ ቫቲካን በመካሄድ ላይ ያለው የአፍሪቃ ብፁዓን ጳጳሳት ይፋዊው ሁለተኛ ሲኖዶስ በሰባተኛው ቀን ውሎው የፍትሕ እና የሰላም ጳጳሳዊ ምክር ቤት የሥራ ሂደት በተመለከተ RealAudioMP3 በቀረበው መግልጫ፣ በአፍሪቃ በመስፋፋት ላይ ስላሉት አዳዲስ የተነጣጠሉ የጴንጠቆስጤ ቡድኖች እያስከተሉት ያለው ችግር ንኡስ ርእስ በማድረግ ከተወያዩ በኋላ፣ የሲኖዶስ አበው በዴሞክራሲያዊት ሬፓብሊክ ኮንጎ ሰላም እንዲረጋገጥ ጥሪ ማቅረባቸው ከሲኖዶስ አዳራሽ የተላለፈልን ዜና ያረጋግጣል።

የአፍሪቃ ዘርፈ ብዙ ችግሮች እና ተስፋዎች በመዳሰ፣ ከምዕራብ ዓለም ጋር ያላት ግኑኝነት በተመለከተ በመወያየት፣ አፍሪቃ ከምዕራቡ ዓለም ጋር ያላት ግኑኝነት በአንዳዊው እና በብቸኛው የምዕራቡ ርእዮት የተጨቆነ፣ የአፍሪቃ ተጨባጩ ሁለ ገባዊ ሁኔታ እግምት ውስጥ የማያስገባ አመለካከት እድትከተል የሚያስገድድ፣ ሚዛኑ ያልጠበቀ ሆኖ እንደሚታይ ከተብራራ በኋላ፣ የምዕራቡ ዓለም የግኑኝነት ውሳኔ ትእዛዝ የተሞላው ኅልዮ በማቅረብ የሚከናወን አፍሪቃን እግምት ውስጥ የማያስገባ የእግዚአብሔር እቅድ የሚጻረር፣ የቤተሰብ የተቀደሰውን ትርጉም የሚቀናቀን፣ ጽንስ ለማስወረድ የሚጋብዝ፣ ሰው ሠራሽ የጽንስ መቆጣጠር ሥልት የሚያስተጋባ መሆኑ ተገልጠዋል።

በመቀጠል በቅርቡ በጊኒ ኮናክሪ የተከሰተው ሁከት ብፁዓን አበው ሲኖዶስ በመጥቀስ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ በዚህች አገር ተከስቶ ያለው ሁከት እና ብጥብጥ ተወግዶ ሰላም እንዲወርድ ያቀረቡት ጥሪ በማስታወስ ምስጋናን አቅርበው፣ በዴሞክራሲያዊት ሬፓብሊክ ኮንጎ በማኅበረ ክርስትያን ላይ የሚሰነዘረው አመጽ በማውገዝ ለዚህች አገር ክርስትያን ህዝብ ትብብራቸውን አቅርበው ለመላይቱ አፍሪቃ ሰላምን ተማጥነዋል።

የአፍሪቃ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤቶች የፖለቲካ ሥልጣን መገልገያ መሣሪያ መሆን እንደማይገባቸው፣ ቁምስናዎች ማንም ዜጋ የሻራ ሃይማኖቶች ሰላባ እንዳይሆን በማሰብ የሁሉም ቤት ክፍት ሆነው መገኘት እንደሚኖርባቸው የሲኖዱስ አበው በማሳሰብ፣ ወንጌልን ለማስፋፋት፣ የአፍሪቃ አገሮች ባህል የሚያገናዝብ እና በወንጌላዊ ባህል እንዲታደስ፣ እርቅ የማነቃቃት ብቃት ሊኖራቸው እንደሚገባም የሲኖዶስ አበው አስገንዝበዋል።

አፍሪቃን እያሰቃየ ያለው ሙስና፣ በፖለቲካ አካላት በመንግሥታት እና አልፎ አልፎ በካቶሊክ የፖለቲክ አካላት ጭምር የሚከናወን መሆኑ ሲኖዶሱ በማብራራት፣ ይኸንን ሁሉ ለመግታት እና ቅን መንገደ የሚያመለክተውን የቤት ክርስትያን ማህበራዊ ትምህርት በሚገባ ማስተላለፍ እና የካቶሊክ የመገናኛ ብዙኃን ይኽ የቤተ ክርስትያን ማኅበራዊ ትምህርት በአፍሪቃ ባህል እንዲሰርጽ እና አስፍሆተ ወንጌል የሚደገፍ የሚያነቃቁ ሆነው መገኘት ይኖርባቸዋል።

በመጨረሻውም የግብረ ሠናይ ማኅበራት በአፍሪቃ ለእድገት የሚሰጡት ድጋፍ ማኅበራዊ እና ሰብአዊ ሁኔታ እግምት የሚያስገባ የአፍሪቃ ባህል፣ ኅብረተሰብ እና አካባቢ የሚያከብር መሆን እንድሚገባው የሲኖዶስ አበው አሳስበዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.