2009-10-08 09:37:04

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክሳዊት ተዋህዶ ቤተ ክርስትያን ፓትሪያርክ ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ለአፍሪቃ ብፁዓን ጳጳሳት ሁለተኛው ሲኖዶስ ያሰሙት ንግግር


የኢትዮጵያ ኦርቶዶክሳዊት ተዋህዶ ቤተ ክርስትያን ፓትሪያርክ ብፁዕ ወቅዱስ ጳውሎስ ለአፍሪቃ ካቶሊክ ቤተ ክርስትያን ብፁዓን ጳጳሳት ሁለተኛው ሲኖዶስ በእንግድነት ተገኝተው ንግግር ማሰምታቸው ሲገለጥ፣ ፓትሪያርክ ብፁዕ ወቅዱስ ጳውሎስ RealAudioMP3 ንግግር ማሰማታቸው ከሲኖዶስ አዳራሽ የተላለፈልን ዜና ያረጋገጣል።

ፓትሪያርክ ብፁዕ ወቅዱስ ጳውሎስ በስም አብ ወወልድ ወንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፣

ክቡራን በዚህ የብፁዓን ካርዲናላት እና ብፁዓን ጳጳሳት ጉባኤ ተሳታፊዎች፣ በዚህ ዓቢይ ሲኖዶስ እንድሳተፍ እና ንግግር እንዳቀርብ የተደረገልኝ የክብር ጥሪ ለእኔ ትልቅ ክብር እና ልዩ እድል ነው። በተለይ ደግሞ፣ ለርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ 16ኛ በናነተ መካከል እንድገኝ ላቀረቡልኝ ጥሪ እና እ.ኤ.አ. ባለፈው ሰነ ወር በሮማ ባካሄድነው የጋራ ግኑኝነት ለአፍርቃ ያላቸው ፍቅር እና ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስትያን ያላቸውን አክብርቶ የሰጡት የግል ምስክርነት በማስታወስም ምስጋናዮን አቅርባለሁኝ”።

“አፍሪቃ በስፋቷ ሁለተኛ ክፍለ ዓለም መሆኗንም ገልጠው፣ በስምምነት እና በእኩንልነት የሚኖሩት የተለያዩ የኅብረ አሕዛብ አገር ነች። ይህ የኅብረ ብዛቱ እዚአብሔር ለአፍሪቃ የሰጣት ጸጋ ነው። የአፍሪቃ ውበት መግለጫም ነው። በሌላ ረገድም አፍሪካ እያንዳንዱ ሕዝብ አለ ቀለም እና ጎሳ ልዩነትም ሁሉም በእኩልነት የሚኖርባት ምድር ነች” ብለዋል።

የሥነ ሰብእ፣ የፍልስፍና እንዲሁም ምሁራን፣ ኢትዮጵያ በጠቅላላ አፍሪቃ የሰው ልጅ መሠረት መሆኗ ያረጋገጣሉ። የኢትዮጵያ መርሃ እለት መሠረት፣ ታሪክ ከአዳም እና ከኖሕ የሚጀምር መሆኑ ያወሳል። ይኽ ማለት ደግሞ ለኛ ኢትዮጲያውያን የፍጥረት አጀማመር፣ ያለንበት ጊዜ መጪው ጊዜ ዛሬም ሁሌም በእግዚአብሔር እና በእርሱ የማዳን ታሪክ አማካኝነት የተመለክተ ነው”።

“የአፍሪቃ ህዝብ ጥንታዊው ክብር የሥልጣኔ ምንጮች ብቻ ባልሆኑት በአክሱም ሐወልት በግብጽ ፒራሚድ፣ በተለያዩ በአፍሪቃ በሚግኙት ጥንታውያን ብራናዎች ዘንድ ተቀርጾ ይገኛል። በመካከለኛው ምስራቅ ይኖር የነብረው ሕዝብ ከሚደርስበት ድርቅ እና እርሃብ ለመላቀቅ በኢትዮጵያ መጠጊያ ያገኝ ነበር። በጠቅላላ አፍርቃ በእርሃብ ለሚጠቃው ህዝብ መጠቂያ ነበረች። ቅዱስ መጽሓፍ እንደሚያረጋገጠውም አይሁዳውያን እና ነቢይ ኤርሚያስ እንደሚለውም በባቢሎናውያን ወረራ ዘመን በኢትዮጵያና በግብጽ መጠለያ እንዳገኙ እንረዳለን። በተመሳሳይ መልኩም ከሄሮዶስ ጭካኔ ለመተረፍ ኢይሱስ ክርስቶስ እና ቅድስት ድንግል ማርያም በግብጽ መጠጊያ እንዳጉኝ ሲረጋገጥ፣ አፍሪቃውያን ሰዎችን እንደሚንከባከቡ የሚያረጋገጥልን ሓቅ ነው። አፍሪቃ በከአሌ ኵሉ እግዚአብሔር ለዘመናት ያመኑ የአማኞች ክፍለ አለም ነች፣ ቅድስት ሳባ ለአገሯ ሕዝቦች ከእስራኤል የተቀበለችውን ብሉይ ኪዳን እንዳስተማረቻቸው እና ከዚያኑ ወዲህ የሙሴ ጽላት በኢትዮጵያ በአክሱም ከተማ ይገኛል”።

“የቅድስት ሳባ ልጅ ሚኒሊክ ሁለተኛ የእርሷን አብነት በመከተል የሙሴን ጽላት ወደ ኢትዮጵያ አፍሪቃ ለማምጣት ችለዋል። የኢትዮጵያዊው ጃንደረባ ታሪክ ወሳኙ ሕግ እና በሙሴ በሚገባ የተደራጀ እምነትን በፍጹም በመኖር እና በሃይማኖት የተሸኘው ባህል ሆኖ ከእስራኤል ይልቅ በኢትዮጵያውያን ሕይወት ዘንድ በሚገባ ይኖር እንደነበር ይመሰክረዋል። ይህኽን ለማረጋገጥ የኢትዮጵያ ህዝብ ታሪክ እና ባህል ያኗኗር ስልት ቀርቦ ማየቱ ይቻላል”።

በግብጽ እሌክሳንድሪያ ቅዱስ መጽሓፍ ከእይሁድ ቋንቋ ውጭ መተርጎሙ እና ይኽ ትርጉም ደግሞ የሰብአ ሊቃውንት ትርጉም ተብሎ የሚጠራ መሆኑ አስታውሰው፣ የአፍሪቃ ህዝቦች ቅዱስ መጽሓፍ እንደሚያመለክተውም ከብሉይ ኪዳን ዘመን ጀምረው፣ በአዲስ ኪዳን ዘመንም በህሊና ሕግ መሠረት ለእግዚአብሔ ሥግደት የማቅረብ ልምድ እንደነበራቸው እናረጋገጣለን”። የኢትዮጵያው ንጉሥ ባልዳሳረ ለኢየሱስ ሕጻን ሥግደት ለማቅረብ ወደ ቤተልሔም መሄዱ እንዱሁም ኢየሱስ በሕማማቱ ወደ ጎልጎታ ተራራ መስቀል ተሸክሞ በመውጣት ላይ እያለ፣ አዲስ ኪዳን እንደሚናገረውም፣ አንድ ከሊቢያ የመጣ ስምዖን ቀረናዊ የተባለው አፍሪቃዊ መስቀሉን እንደተሸከመም እንገነዘባለን። ልብ እንበል በ 34ኛው ዓ.ም. አንድ ኢዮጵያዊው ጃንደረባ እንደ ሙሴ ሕግ መሠረት ለእግዚአብሔር ሥግደት ለማቅረብ ወደ ኢየሩሳሌም መሄዱ እና በመንፈስ ቅዱስ ትእዛዝ መሠረትም በፊሊጶስ መጠመቁ እንረዳለን። የተጠመቀው ኢትዮጵያዊው ጃንደረባ ወደ አገር ተመልሶ ክርስትናን ሰበከ፣ ይህ ደግሞ ኢትዮጵያ ከእስራኤል ቀጥላ በክርስቶስ ያመነች ሁለተኛ አገር እና የኢትዮጵያ ቤተ ክርስትያን በአፍሪቃ የመጀመሪያ ቤተ ክርስትያን ለመሆን እንዳበቃት የሚያረጋገጥ ታሪክ ነው”።

“በመጀመሪያ የእምነት ዘመኖች ታሪክ፣ የአፍሪቃ የክርስትና መለያ ይኽም አፍሪቃውያን ዘወትር ፍቅር እና ለአዲስ ኪዳን ያላቸው አክብሮት በጥልቅት እንደሚኖሩት ያመለክትልናል። አፍሪቃ በአፍሪቃ እና በመላው ዓለም የሚከበሩት የታላላቅ የቤተ ክርስትያን ምሁራን እና አበው የሚባሉት፣ የቅዱስ አጎስጢኖስ፣ የቅዱስ ተርቱሊያን የቅዱስ ቅጵሪያኖስ የቅዱስ አናስታዚዮ የቅዱስ ቄርሎስ አገር ነች፣ ዓለም በሞላ በታልቅ ችሎታው የሚያደንቀው የመዝሙር ደራሲው ቅዱስ ያሬድ አፍሪቃዊ፣ የኢትዮጵያ ልጅ፣ ድርሰቶቹ ኢትዮጵያ በዓለም ዙሪያ እንድትታወቅ ያደረጋት ነው። የእነዚህ የቤተ ክርስታይን አበው ድንቅ ሥራዎች የአፍሪቃን መግለጫ እና መለያ ናቸው” ብለዋል።

አፍሪቃ የመጀመሪያ የመጽሐፍ ቅዱስ ቀኖና የተደነገገባት ምድር፣ የሰሜን አፍሪቃ ሰማዕታት እንዲሁም በተለያዩ አገሮች ስደት እና መከራ ይደርስባቸው የነበሩት ክርስትያኖች በአፍሪቃ መጠጊያ ያገኙ እንደነበር እና በዚህች ክፍለ ዓለም በሰላም ለመኖር መቻላቸውንም ታሪክ ይመስክራል፣ ኢትዮጵያ በኤውሮጳ ስደት እና መከራ ይደርስባቸው ለነበሩት ክርስትያኖች መሬት መሆኗ፣ የነዚህ ክርስትያኖች የኢትዮጵያ ክልሎች ተጠብቆ እና ተከብሮ የሚገኝ የመቃብር ሥፍራ ይመሰክረዋል”።

“በኢትዮጵያ የቅዱስ መስቀል ትሩፋት ጎሸን ተራራ ተብሎ በሚጠራው ሥፍራ ይገኛል፣ የአፍሪቃ ክርስትያኖች መስቀልን የተሸከሙ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስትያን በነበረው የኮሙኒዝም ሥርዓት ወቅት ስደተ እና መከራ እንደደረሰባት፣ ብዙ የደም ምስክርነ የተከፈለባት ስትሆን፣ ብፁዕ ወቅዱስ ፓትሪያርክ ተዮፊሎስ ከሳቸውም በፊት በቅኝ ግዛታ ዘመን ሰማዕትነት የተቀበሉት ብጹዕ ወቅዱስ ጴጥሮስ” እሳቸውም መጀመሪያ “በእሥር እንደተሰቃዩ እና ለብዙ ዓመታት ስደት መዳረጋቸውም” ነግረው “የኮሙኒዝም ሥርዓት ተገርስሶ ፓትሪያርክ ሆኜ ከተሾምኩኝ ወዲህ የወደመውን ዳግም ለመገንባት ዓቢይ ኃላፊነት እንዳለን ተገንዝበን በእግዚአብሄር በገዳማውያን እና በሁሉም አማኞች ጸሎት አማካኝነት እየተወጣን ነው” ብለዋል።

“አፍሪቃ እምቅ ኃይል ያላት የለ መሬት እና በተፈጥሮ ሃብት የታደለች የተስተካከለ ውብ ያየር ጸባይ፣ ገና ላገልግሎት ያልዋለ ሃብት የተሸከመ መሬት ባለቤት፣ ብዙዎች ዓይናቸውን የሚጥሉባት” መሆኗ ገልጠው፣ “በተለያዩ አገሮች የሚታየው እድገት እና ብልጽግና የአፍሪቃ ድካም እና ተፈጥሮ ሃብት መሠረት የተረጋገጠ ነው ካሉ በኋላ፣ አፍሪቃውያን ብዙ ቅዱስ ሥራዎች ለዓለም አከናውነዋል፣ ባንጻሩ ግን ዓለም ለአፍሪቃ ምን አደረገላት? ቅኝ ግዛት ደርሶባታል፣ የተፈጥሮ ሃብቷ ተበዝብዘዋል፣ የተፈጥሮ ሃብቷን እንጂ አፍሪቃ ለምታደርገው የእድገት ጎዳና ለመደገፍ የሚያስብ ሃብታም አገር እንደሌለ፣ የአፍሪቃ አገሮች በተለያየ መልኩ ብዙ ማህበራዊ ፖለቲካዊ ኤኮኖሚያዊ እና መንፍሳዊ ነክ ችግሮች ተጋፍጠው ይገኛሉ፣ የአፍሪቃ ህዝብ በዓለም አንጻር ሲታይ በዝቅተኛ ኑሮ የሚተዳደር፣ የህዝቡ የኑሮ ደረጃ ከዕለት ወደ ዕለት እያሽቆለቆለ፣ የትምህርት እድል እጥረት ወጣቱን ምንኛ እይጎዳ መሆኑም፣ አለ ሕንጸት እና የትህምርት ዕድል ማንም ህዝብ እና አገር ዕድገት ለማረጋገጥ አይችልም” ብለዋል።

“ብዙ ጥረት እየተደረገ ቢሆንም ቅሉ አፍሪቃን በእጅጉ እያሰቃየ ያለው የኤይድስ በሽታ ለመቆጣጠር እጅግ አዳጋች እየሆነ መምጣቱንም ገልጠው፣ በአፍሪቃ የሚታዩት ችግሮች በተቻለ መጠን ይቃለል ዘንድ የተለያዩ የአፍሪቃ አቢያተ ክርስትያን ምክር ቤቶች የተቻላቸውን ሁሉ ለማድረግ መነሳታቸው” መስክረው፣ “በተለይ ደግሞ አክራርያን እና ፀንፈኞች የሚቀሰቅሱት ችግር ለማገድ አቢይ ጥረት እያደረጉ ናቸው፣ ይኸንን ሁሉ እግብ ለማድረስ የሃይማኖት መሪዎች እና ምእመናን በጠቅላላ እጅ ለእጅ ተያይዘው መሥራት ይገባቸዋል” ብለዋል።

ያለው ትውልድም ይሁን የሚመጣውም ትውልድ ከፍሎ የማይዘልቀው አፍሪቃ ያለባት የውጭ የብድር ጫና” ዘክረው፣ “በአፍሪቃ የሚታዩት ግጭቶች እና ሕፃን ወታደሮች የሚሳተፉባቸው ጦርነቶች፣ የሕገ ወጥ ስደተኞች ጸዓት የመሳሰሉት አፍሪቃን እያሰቃዩ ያሉት ችግሮች” አስታውሰው፣ “የአለም አቀፍ የሰብአዊ መብት እና ፈቃድ ውሳኔ እንደሚያመለክተው ከአሥራ ሥምንት ዓመት በታች በወትድርና ዓለም መቀጠር እንደሌለበት ሲያመለክት፣ ሆኖም ግን ይኽ ሕግ በአሁኑ ወቅት ተጥሶ ይገኛል። ይህ ጉዳይ ጨርሶ እንዲወገድ በጠቅላላ የአፍሪካ አቢያተ ክርስትያን በአንድነት ድምጻቸውን ከፍ በማድረግ ማሰማት ይኖርባቸዋል። ይኸንን አጋጣሚ በመጠቀም ሁሉም የሃይማይማኖት መሪዎች በጋራ ለሰላም እና ለአፍሪቃ እግዚአብሔር የሰጣት የተፈጥሮ ሃብት እንዲጠበቅ እና ሕይወት እና የሕጻናት ሕይወት እንዲጠበቅ ተባብረው በጋራ ይሠሩ ዘንድ” አደራ ብለዋል።

“በአፍሪቃ መሠረታዊ የሰው ልጅ ፍላጎት እንዲከበር” በማሳሰብ “ምንም’ኳ የቅኝ ግዛቱ ሥርዓት ያከተመለት ቢሆንም ቅሉ፣ ገና አሁንም የሃብታም አገሮች ጥገኞች የሆኑ የአፍሪቃ አገሮች እንዳሉም” አስታውሰው “ይህ ደግሞ አፍሪቃ ለብዙ ችግሮች ከማጋለጡም አልፎ ምሁራን እና ድንቅ ምርጥ ልጆቿ ለስደተ በመዳረግ ለከፋው ችግር እንድትጋለጥ እያደረገ ነው። እነዚህ የተጠቀሱት ጉዳዮች ብፁዓን ካርዲናላት እና ጳጳሳት ይወያዩባቸው ዘንድ” አደራ ብለዋል። እኛ ይላሉ ብፁዕ ፓትሪያርክ ጳውሎስ፣ “መልካም የሆነው መደገፍ የሰውን ክብር እና ፍቅርን የሚጻረር የሚነዛውን ሁሉ ለመቃወም የኃላፊነት ግዴታ አለብን። ክርስትያኖች የፍትህ የሰላም የእርቅ እና የእድገት መልእክተኞች ይሆኑ ዘንድም” አሳስበው፣ “በአፍሪቃ እነዚህ የላቁ እሴቶች እግብር ላይ እንዲውሉ የቅዱስ ኤጂዲዮ ማኅበር ቆራጥ እና ትህትና የተሞላው ጥረት እንደ አብነት ጠቅሰው፣ የሃይማኖት መሪዎች የማኅበራዊ ጉዳይ ብቻ ሳይሆን የሰዎች መንፈሳዊ ጥያቄዎች ምላሽ የመስጠ ኃላፊነት እንዳለባቸው እና የማኅበራዊ የመንፈሳዊው ተነጣጥለው መሄድ የለባቸውም” ብለዋል። “የሰብአዊ መብት ጥበቃ ሰላም ፍትሕ ለማነቃቃት ልኡካነ ወንጌል አበክረው መሥራት ይገባቸውል” ብለዋል።

“የአፍሪቃ አቢያተ ክርስትያን በእግዚአብሔር ኃይል እና በመንፈስ ቅዱስ ለቤተ ክርስትያን ቃንቋ ድምጽ መሆን ይገባቸዋል፣ ለቤተክርስትያን ደህንነት ከማን ጋር እና እንዴት መነጋገር እንዳለበትም ጠንቅቀው ማወቅ አለባቸው” ካሉ በኋላ፣ “በዚህ በአፍሪቃ የካቶሊክ ቤተ ክርስትያን ብጹዓን ጳጳሳት ሁለተኛው ሲኖዶስ በእንግድነት እንድሳተፍ በመጋበዜ እጅግ ደስተኛ ነኝ፣ አፍሪቃዊ ነኝ፣ ቤተ ክርስያኔም የሰማዕታት የቅዱሳን የገዳማውያን ጥንታዊት የአፍሪቃ ቤተ ክርስትያን ነች፣ ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ይኽ ጥሪ ስላቀረቡልኝ አመሰግንዎታለሁኝ። ስለ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል እንናገር፣ ኢየሱስ በሕጻንነቱ ከማርያም ጋር በግብጽ እንደነበር ሁሉ፣ ሁንም ወደ አፍሪቃ ይመለሳል፣ ከእርሱም ጋር ሰላም ምህረት እና ፍትሕ ወደ አፍሪቃ ይመለሳል። እግዚአብሔር የአፍሪቃን ቤተ ክርስትያን እና አገልጋዮቿንም ይባርክ አሜን። በማለት ያሰሙትን ንግግር ደምድመዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.