2009-10-08 09:33:31

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ለኢትዮጵያ ኦርቶዶስክ ተዋህዶ ቤተ ክርስትያን ፓትሪያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ያቀረቡት ሰላምታ


ቅ. አ. ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ በዚህ በቫቲካን በመካሄድ ላይ ባለው ሁለተኛው ይፋዊ የአፍሪቃ ብፁዓን ጳጳሳት ሁለተኛው ሲኖዶስ በእንግድነት በመሳተፍ ላይ ለሚገኙት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክሳዊት ተዋህዶ ቤተ ክርስትያን ፓትሪያርክ ለብፁዕ RealAudioMP3 ወቅዱስ ጳውሎስ ለየት ባለ መልክ ሰላምታ ሲያቀርቡ፣ “በዚህ የአፍሪቃው ሁለተኛ በእንግድነት እንዲሳተፉ ያቀረብኩሉዎትን ጥሪ ተቀብለው አወንታዊ ምላሽ ሰጥተው እዚህ በመገኘትዎት በእኔ እና በሁለተኛው የአፍሪቅ ብፁዓን ጳጳሳት አበው ስም ከፍ ያለ ምስጋናየን አቀርብልዎታለሁኝ፣ የእርስዎ እዚህ መገኘትም የአፍሪቃ ጥንታዊት እና በባህል ሃብታም ለሆነቸው ቤተ ክርስትያን አንደበተ ርቱዕ እና ስሜት የሚነካ ሕያው ምስክርነት ነው። በግብረ ሃዋርያት ምዕራፍ 8 ከቁጥር 26 እስከ 40 እንደምናነበው በሐዋርያት ጊዜ የክርስቶስ የድህነት መልእክት ቀርበው ከሐዋርያት አንደበት ያዳምጡ ከነበሩት አሕዛብ ውስጥ ከኢትዮጵያ የመጡ ጭምር ይገኙባቸው እንደነበርም እንረዳለን፣ የዚህ ሕዝብ ለወንጌል ያለው ታማኝነት አሁንም ቀጣይ ሆኖ ለእግዚአብሔር የፍቅር ትእዛዝ ታዛዥ መሆኑ እና እርስዎም ቀድመው እንዳሉት ይኽ ሕዝብ ስደት መከራ ተሻግሮ ስለ ክርስቶስ ሰማዕትነትንም በመቀበል እምነቱን በመመስከር እምነቱን አቅቦ ይኖራል”።

“ከእግዚአብሔር የተቀበልነውን የተፈጥሮ ጸጋ እና የሁሉም የእግዚአብሔር ልጆች ክብር በመጠበቅ ከእግዚአብሔር ፈቃድ ጋር በሚጣጣም ይኸንን የሚከተል ኅብረተሰብ ለመገንባት ከሕይወት የማይነጠል ስብከተ ወንጌል አስፈላጊ ነው” በማለት የገለጡን ሀሳብ ጠቅሰው “እንደምንረዳውም በክርስቶስ እርቅ የሚቻል ነው፣ በእርሱም ፍትሕ ድል ይነሳል ዘላቂነት ያለውም ሰላምም ይረጋገጣል። ይኽንን ተስፋ ለማብሰር ነው የተጠራነው። የአፍሪቃ ህዝቦች ዛሬ ይኸንን ተስፋ ነው በጉጉት የሚጠባበቁት” ብለዋል።

በመጨረሻም “ከወንጌል የሚመነጨውን ተስፋ ለመመስከር እንድንችል ቤተክርስትያኖቻችን በመቀራረብ የመንፈስ ቅዱስ ስጦታ ወደ ሆነው አንድነት ያቀኑ ዘንድ እንጸልይ፣ የሁሉም የአፍሪቃ ህዝቦች ምሉእነቱ የተረጋገጠ ሰብአዊ እድገት እውን እንዲሆን የአፍሪቃ ኅብረተሰብ ምሰሶ የሆኑትን ቤተሰብች ለመደገፍ የአፍሪቃ የነገ ሕይወት ብሩህ ተስፋ የሆነውን ወጣቱን ትውልድ ለማነጽ ቅንነት ምሉእነት እና ትብብር የሚለው ኅብረትሰብ ለመገንባት ተባብረን በጋራ እንሥራ፣ በሚቀጥለው ሳምነት በጋራ በምናረጋገጠው ውሳኔ መሠረት በመላይቱ አፍርቃ የክርስቶስ ተከታዮች ለሆኑት የቅንነት የምህረት እና የሰላም እንዲሁም የመጪውን ትውልድ ጉዞ የሚመራው ብርሃን ምስክሮች እና አብነት ለመሆን ያብቃን በማለት አክለውም ደግሜ እዚህ በተገኝተው አገቢ እና ብቃት ያለው ስላሰሙት ንግግር ከፍ ያለ ምስጋናዮን አቀርባለሁኝ፣ የእርስዎ በዚህ የአፍሪቃ ሁለተኛው ሲኖዶስ መገኘት ለቤተ ክርስትያኖቻችን ቡራኬ ነው” በማለት ቅዱስ አባታችን ያቀረቡትን ሰላምታ ደምድመዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.