2009-10-07 17:03:26

የር.ሊ.ጳ. ኣስተምህሮ


ቅ.ኣ.ር.ሊ.ጳ.በ.16ኛ ዛሬ ረፋድ እንደወትሮኣቸው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለተሰበሱት በብዙ ሺ ለሚቆጠሩ ምእመናንና ነጋድያን የተለመደውን ሳምንታዊ የዕለተ ሮብ ኣጠቃላይ ትምህርተ ክርስቶስ ኣቅርበዋል።

ጉባኤውን በጸሎት ከከፈቱ በኋላ የሚከተለው ቃለ እግዚአብሔር ከመዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ አንድ ተነበበ።

1 በክፉ ሰዎች ምክር የማይሄድ፥ በኃጢአተኞችም መንገድ የማይቆም፥ በፌዘኞች ወንበር የማይቀመጥ የተባረከ ነው። 2 እንዲህ ያለ ሰው፣ በእግዚአብሔር ሕግ ደስ ይለዋል፥ ሕጉንም ቀንና በሌሊት ያሰላስለዋል። 3 ስለዚህም እርሱ፣ ፍሬዋን በየወቅቱ እንደምትሰጥ፥ ቅጠልዋም እንደማይረግፍ በፈሳሽ ውኃ ዳር እንደ ተተከለች ዛፍ ይሆናል፤ የሚሠራውም ሥራ ሁሉ ይሳካለታል። 4 ክፉዎች ግን እንዲዚህ አይደሉም፥ እነርሱ ነፋስ ጠርጎ እንደሚወስደው ገለባ ናቸው። 5 ስለዚህ ክፉ ሰዎች፣ በፍርድ ቀን ጸንተው አይቆሙም፥ ኃጢአተኞችም በጻድቃን መካከል አይገኙም። 6 ምክንያቱም እግዚአብሔር የጻድቃንን መንገድ ያውቃልና፥ የክፉዎች መንገድ ግን ትጠፋለች።

ቅዱስነታቸው በዛሬ ትምህርታቸው ከነገ ወዲያ እአአ ጥቅምት 9 ቀን 2009 ዓ.ም የሚታወሰው ቅዱስ ዮሓንስ ሊዮናዲ ከሞቱ አራት መቶ ዓመት መምላቱን አስመልክተው አስትምረዋል። ከዚህ በመቀጠል በተለያዩ ቋንቋዎች ካቀረብዋቸው ትምህሮቶች ለእንግሊዘኛ ተናገሪዎች የሰጡትን ትምህርት እናቀርብላችኋለን።

ውድ ወንድሞቼና እኅቶቼ፣ ይህ ሳምንት ቅዱስ ዮሐንስ ለዮናርዲ ከሞቱ 400ኛ ዓመት ያመለክታል። ቅዱሱ መደበኛ የእመ አምላክ ካህናት ማኅበር መሥራች ናቸው። የእነዚህ ካህናት የስብከተ ወንጌል መንፈሳዊ ቅናት በፕሮፓጋንዳ ፊደ የሚታወቀው የአሕዛብ ስብከተ ወንጌል ቅዱስ ማሕበር መቋቋም ምክንያት ሆነዋል። ቅዱስ ዮሓንስ ሉካ በሚባል ከተማ አከባቢ ተወለዱ። በፋርማሲ ትምህርት ከሠለጠኑ በኋላ በጊዜው ለነበሩ ሰዎች የእግዚአብሔር መድኃኒት ለመስጠት መዓርገ ክህነት ተቀብለው በትጋት አገለገሉ። በዚያ ጊዜ የቤተ ክርስትያንን ሕይወት ለመለወጥና ለማሳደስ ብርቱ ጥረት ይደረግ ስለነበረ፣ ቅዱስ ዮሓንስ የስብከታቸው ማእከልና የሁሉ ነገር መመዘኛ ያደረጉት የኢየሱስ ክርስቶስን መስቀል ነበር። ቅዱሱ እውነተኛ የቤተ ክርስትያን ሕይወት ለውጥ የሚመነጨው በክርስቶስ ባለ እምነትና ለቤተ ክርስትያኑ ባለ ፍቅር መሆኑን በደንብ ተገንዝበው ነበር። ወጣቶችን ትምህርት ክርስቶስ ለማስተማር እንዲሁም የክርስትያን ሕይወትንና ኑሮን ለማሳደስ የስብከተ ወንጌል ሥራን ለማስፋትና ለማነቃቃት የገፋፋው የኢየሱስ ፍቅር ነበር።

ሌላው ቅዱስ ዮሐንስ በልበ ምሉነት ያመነው ነገር ቢኖር የሰው ልጅ ሁሉ መመዘኛ ክርስቶስ መሆኑን ነው፣ ከዚህ የተነሣ የኅብረተሰብ ቅድስናንና ለውጥ ለማጐልበት በተጨባጭ እውነትና መንፈሳዊ ቅናት ይሠራ ነበር። በዚሁ ዓመት ካህን በምናስብበት ጊዜ የዚህ ታላቅ ስብከተ ወንጌላዊ ምስል ካህናትንና ምእመናንን እንደገና በአዲስ መንፈስ ከክርስቶስ ለመጀመር እንዲያበራላቸው፣ ጥሪአቸውን በጋለ ስሜትና ጉግት እንዲቀበሉ ይርዳቸው። በማለት ስለቅዱስ ዮሐንስ ሊዮናርዲ ካሳሳሰቡ በኋላ፣ በመጨረሻ ከተለያዩ የዓለም ክፍሎች ትምህርታቸውን ለመክታተል ለመጡ ምእመናንና ነጋድያን በተለያዩ ቋናቋዎች ሰላምታ አቅርበውና ኣመስግነው በማካሄድ ላይ ያለው የአፍሪቃ ጳጳሳት ሲኖዶስ ስኬታም እንዲሆን በጸሎት እንዲተባበርዋቸው በማማጠን ሓዋርያዊ ቡራኬ በመስጠት ኣሰናብተዋቸዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.