2009-10-05 14:27:25

የጎፍር መጥለቅለቅ አደጋ በኢጣሊያ


በኢጣሊያ መሲና ከተማ የተከስተው የጎርፍ መጥለቅለቅ አደጋ በሰው እና በንብረት ላይ አቢይ ጉዳት አስከትለዋል፣ እስከአሁን ድረስ የተፈጥሮ እና ሰው ሰራሽ የአደጋ የመከላከያ ቢሮ ከሰጠው መገልጫ ለ RealAudioMP3 መረዳት እንደተቻለው 35 ሰዎች የሞት 95 ደግሞ የመቁሰል አደጋ እንደረሰባቸው እና ወደ አርባ የሚገመቱት ገና በመፈለግ ላይ ናቸው።

በዚህ ኃይለኛው ዝናብ ባስከተለው የውሃ መጥልቅለቅ እና የመሬት መናድ አደጋ የተጎዳው ሕዝብ ለመርዳት ፈጥኖ ደራሽ የአደጋ የመከላከያ ኃይል አለ ምንም እረፍት የተሰወሩትን በመፈለግ ላይ እንደሚገኝ ሲነገር፣ የኢጣሊያው መራሄ መንግሥት ሲልቪዮ በርሉስኮኒ የተጎዳውን ክልል እና ህዝብ መጎብኘታቸውም ተገልጠዋል።

የደረሰው የሰው እና የንብረት ጉዳት ለመገምገም በመሲና የመንግሥት ወኪል ጽ/ቤት እና የክልሉ የአደጋ የመከላከያ ቢሮ በመተባበር እየሠሩ መሆናቸውም ለማወቅ ሲቻል፣ ይህች ከተማ ለተፈጥሮ አደጋ በቀላሉ ከሚጋለጡት የኢጣልያ ከተሞች ውስጥ አንዷ ስትሆን የዚህ አይነት አደጋ እንዳያጋጥም ቀድሞ የመከላከሉ ጉዳይ ማነቃቃት የኢጣሊያ የፈጥኖ ደራሽ የአደጋ ተቆጣጣሪ ኃላፊ ጉይዶ በርቶላሶ ጠቅሰው፣ የተጎዳውን ሕዝብ መደገፍ እና ዳግመ ግንባታውን ማፋጠን ብቻ ሳይሆን ቀድሞ ከተፈጥሮ አደጋ የመከላከሉ ስልት በከተማይቱ መረጋገጥ ይኖርበታል ብለዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.