2009-10-05 14:25:31

የኤውሮጳ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤቶች ኅብረት


በፓሪስ ለአራት ቀናት የተካሄደው የኤውሮጳ የብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤቶች ኅብረት ጉባኤ ትላትና ተፈጽሟል።

በኤውሮጳ ቤተ ክርስትያን ለውጥ እንደማትሻ ተደርጎ የሚነዛው እንዲሁም አይሆንም RealAudioMP3 እምቢ ባይ ነች ተብሎ ከፖለቲካው በመገናኛ ብዙሃን እና በባህል ጉዳይ የሚሰጣት መግለጫ እውነት የሌለው መሆኑ ትላንትና የጉባኤው መዝጊያ ያረገውን መሥዋዕተ ቅዳሴ የመሩት የፓሪስ ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ ኣቡነ አንድረ ቪንግት ትሮይስ ባሰሙት ስብከት መግለጣቸው ሲነገር፣ በህዚህ ቤተ ክርስትያን እና መንግሥታት በሚል ርእስ ሥር ለአራት ቀን በተካሄደው የኤውሮጳ ብጹዓን ጳጳት ምክር ቤት ኅብረት ጉባኤ የኢጣሊያ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ሊቀ መንበር የጀኖቫ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ ካርዲንል አንጀሎ ባኛስኮ ር.ሊ.ጳ. እና የመገናኛ ብዙሃን በሚል ርእስ ሥር ለጉባኤው ባሰሙት ንግግር፣ ቅዱስ አባታችን ከለፈብራውያን ጋር ያካሄዱት ግኑኝነት፣ በቅርቡ በአፍሪቃ ያካሄዱት ሓዋርያዊ ጉብኝት እንደ አብነት በመጥቀስ የመገናኛ ብዙሃን ሁኔታውን በሙላት ከማንበብ ይልቅ በመቆንጸል ለነርሱ በሚያመቻቸው መልክ በማንበብ የሰጡት መግለጫ እና ያሰራጩት ዜና ቤተ ክርስትያንን የማይገልጥ ነው ብለዋል።

ቤተ ክርስትያን ስለ ቤተሰብ፣ ድኾች፣ የተናቁት የተነጠሉት በተመለከተ የምትሰጠው፣ መፍነሳዊ፣ ሰብአዊ አገልግሎት ከመሥራችዋ በተቀበለቸው ጥሪ መሠረት መሆኑ ገልጠው፣ የማንኛውም ዓይነት ፖሊትካ አንጸባራቂ ደጋፊ ሳትሆን የእግዚአብሔር የመዳን እቅድ አብሥሪ ነች ካሉ በኋላ፣ ኤውሮጳ የኤኮኖሚ እና የፖሊቲካ ኅብረት የሚረጋገጥባት ብቻ ሳትሆን፣ ባህልዋ ክርስትያናዊ መሠረት እንዳለው የማይክድ ባህል ለኅብረቷ ጽናት መሆኑ በስፋት አብራርተዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.