2009-10-05 18:08:36

የሲኖዶስ የመጀመርያ ዕለት ውሎ


ዛሬ ከቀትር በኃላ በሮማ ቫቲካን ውስጥ የአፍሪቃ ካቶሊካውያን ጳጳሳት ልዩ ሲኖዶስ በቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ በይፋ ተከፍተዋል ።

ቅዱስነታቸው የአፍሪቃውያን ጳጳሳት ልዩ ሲኖዶስ ከአፍሪቃውያን አብረው ሥርዓተ ጸሎት በማድረግ የከፈቱት ሲሆን ሲኖዶሱ በመልካም ተጀምሮ እንዲሁ እንዲፈጸም ኩሉ እግዝአብሔር እንለምን ብለዋል ።

የአፍሪቃ ቤተክርትያን በዕርቅ ፍትህ እና ሰላም አገልግሎት የሚል የሲኖዶሱ መሪ ሐሳብ አስታውሰው ክፍለ ዓለሚቱ ላይ ሰላም እንዲወርድ እድገት እና ብልጽግና እንዲገኝ ያላችውን ከፍተኛ ገልጠዋል ።

ብፁዓን የአፍሪቃ ጳጳሳት ለሶስት ሳምንት ያህል በሚይካሄዱት ሲኖዶድ እግዝአብሔር በምንፈስ ቅዱስ እንዲያበራላቸው እና እሱ ፍቅር በመሆኑ መስናክሎች ሁሉ ይከፍታል ብለዋል።

ከአስራ አምስት ዓመታት በፊት 1994 እኤአ የአፍሪቃ ሲኖዶስ እንዲጀመር ያደረጉት የእግዝአብሔር አገልጋይ ነፍሰሄር ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ አስታውሰዋል ።

ርእሰ ሊቃነ ጳሳት ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ የመጀመርያ ይአፍሪቃ ጳጳሳት ሲኖዶስ ሲጀመር የአፍሪቃ ትንሣኤን ተስፋ ሲኖዶስ ያሉትን አስታውሰው ለጳጳሳቱ መልካም የሲኖዶስ ግዜ ተመኝተውላቸዋል ።

ከርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ በኃላ የተናገሩት ከሊቃነ መናብርት አንዱ የሆኑ ብፁዕ ካርዲናል አሪንጸ ናቸው ። ብፁዕ ካርዲናል አሪንጸ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ ላደረጉት ንግግር እና ለአፍሪቃ ክፍለ ዓለም ያላቸውን ከፍፍተኛ አባታው ሐሳቢነት አምስግነዋል ።

በቅድስት መንበር የጳጳሳት ጉባኤ ሊቀመንበር ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ አቡነ ኒኮላ ኤተሮቪች የአፍሪቃ ቤተክርስትያን ወቅታዊ ሁኔታ አስመልክተው ረጂም መግለጫ የሰጡ ሲሆን ፡በጋና የኬይፕ ኮስት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ ካርዲናል ፒተር ኮድዎ አፕያህ ታርክሰን የአፍሪቃ የኤኮኖሚ ፖሊቲካ እና ማኅበራዊ ሁኔታ በዝርዝር ለሲኖዶሱ ሪፖርት አቅርበዋል በመጨረሻም በርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ መሪነት ጸሎት ተደርጎ የከቀትር በፊት ጉባኤው ፍጻሜ ሆነዋል።

አሁን ከዚህ በመቀጠል የምታዳምጡት ሊቀ ጳጳሳት ዘካቶሊካውያን ኢትዮጵያ ብፁዕ አቡነ ብርሃነየሱስ ሱራፊኤል ሲኖዶሱ ትኩረት በመስጠት የሰጡት አስተያየት ይሆናል ።

RealAudioMP3







All the contents on this site are copyrighted ©.