2009-10-05 14:24:12

ቅዱስ ፍራንቸስኮስ ዘ አሲዚ


እ.ኤ.አ. ጥቅምት 4 የኢጣሊያው ጠባቂ ቅዱስ ፍራንቸስኮስ ዘ አሲዚ ዓመታዊ ክብረ በዓል ምክንያት በማድረግ ሲካሄድ የሰነበተው መንፈሳዊ ባህላዊ እና አውደ ጥናቶች ትላትና ባረገው መስዋዕተ ቅዳሴ መጠናቀቁ ተገለጠ። RealAudioMP3 ቅዱስ ፍራንቸስኮስ በሰማይ የተወለደበተ ቀን የሚዘከርበት፣ የኢጣልያ ጠባቂ ቅዱስ ተብሎ በቤተ ክርስትያን የተሰየመበት 70 ኛው ዓመት፣ እንዲሁ የቅዱስ ፍራንቸስኮስ ማኅበር የተመሠረተበት 800ኛው ዓመት ምክንያት ክብረ በዓሉ እጅግ ከፍ ብሎ እኛ ደምቆ ተከብሯል።

ቀኑን ምክንያት በማድረግ በአሲዚ በሚገኘው ጳጳሳዊ የቅዱሳን እመቤት ቅድስት ድንግል ማርያም ቤተ ክርስትያን በቀረበው መሥዋዕተ ቅዳሴ ከኢጣሊያ እና ከኢጣሊያ ውጭ የመጡ ምእመናን መሳተፋቸው የዚህ ጳጳሳዊ የቅዱሳን እመቤት ቤተ ርክስትያን ጠባቂ ኣባ ፋብሪዚዮ ሚላዞ ከቫቲካን ረድዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ ገልጠው፣ ቅዱስ ፍራንቸስኮስ ከዚህ ዓለም በሞት የተለየበት ዕለት እ.ኤ.አ. ጥቅምት 3 ቢሆንም በቤተ ክርስትያን ባህል መሠረት በሰማይ የተወለደባት ጥቅምት 4 መሆኑ አብራርተው፣ የቅዱስ ፍራንቸስኮስ ትሩፋት አሲዚ በሚገኘው በቅዱስ ዳሚያኖ ቤተ ክርስትያን እንዳረፈም ገልጠው፣ በዚህ ዓለማችን ሰላም ፍቅር እና አንድነት በተጠማበት ወቅት የቅዱስ ፍራንቸስኮስ አማላጅነት እጅግ ያስፈልጋል ብለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.