2009-10-02 14:35:35

የጦር መሣሪያ ትጥቅ በማራገፍ ለሰላም መሥራት


የቅድስት መንበር የውጭ ግኑኝነት ጉዳይ ዋና ጸሃፊ ብፁዕ ኣቡነ ዶሚኒክ ማምበርት እ.ኤ.አ. መስከረም 24 ቀን 2009 ዓ.ም. በኒው ዮርክ በተካሄደው በተባበሩት መንግሥታት ጠቅላይ ጉባኤ ተገኝተው ባሰሙት ንግግር፣ RealAudioMP3 ስለ ሰላም ለመሥራት ተቀዳሚው እና ዋነኛው እርምጃ የጦር መሣሪያ ትጥቅ መፍታት እና እየተስፋፋ በመሄድ ላይ ያለው የኑክሊየር ጦር መሣሪያ ሽቅድድም ጨርሶ ማስወገድ ነው ብለዋል።

እነዚህ ሁለት አንገብጋቢ እና ዓበይት ውሳኔዎች እግብር ላይ ይውሉ ዘንድ ቅድስት መንበር መንግሥታት ለማነቃቃት አበክራ እንደምትሠራም በዚህ አጋጣሚ ደግመው አስታውቀዋል።

በኑክሊየር የጦር መሣሪያ ለመደለብ አንዳንድ መንግሥታት የተያያዙት ሂደት ለመቆጣጠር የሚያስችል የስልት እጥረት እየታየባቸው መሆኑ እና የጦር መሥሪያ የጸጥታ እና የደህንነት ብሎም የሰላም ዋስትና ነው ተብሎ የሚነዛው ምክንያት፣ ኢምክንያታዊ መሆኑ በማስረዳት የተባበሩት መንግሥታት የጸጥታ እና የደህንነት የበላይ ምክር ቤት የጦር መሣሪያ እና የኑክሊየር ጦር መሥሪያ መፍታት ውሳኔ በማነቃቃት እና በሙላት በመደገፍ ይህ ውሳኔ በሁሉም መንግሥታት ዘንድ ገቢራዊ ሆኖ ከአደገኛ የጦር መሣሪያ ነጻ የሆነ ሰብአዊነት የተካነው ዓለም ለማረጋገጥ እንዲችሉ ከመቼውም በበለጠ ከፍተኛ ጥረት እንዲያደርግ አደራ በማለት ቅድስት መንበር የጸጥታ እና የደህንነት ዋስትና የኑክሊየር የጦር መሣሪያ ባለቤትነት የሚያረጋገጠው መሆኑ የሚገልጠው የወታደራዊ መሠረታዊ መመሪያ ከእውነት የራቀ መሆኑ ገልጠው፣ በአለም ዓቀፍ ደረጃ የኑክሊያር ጦር መሣሪያ ሙከራ እገዳ እንዲደረገ የሚያዘው መመሪያ ገና በ ዘጠኝ አገሮች መንግሥታት ተቀባይነቱ ያልተረጋገጠ ቢሆንም ቅሉ ውሳኔው በሁሉም አገሮች ጸድቆ ወቅታዊው ዓለም ከኑክሊየር የጦር መሣሪያ ነጻ የሆነ የሰላም ባህል የሚጎላበት ለማድረግ ሁሉም ይተጋ ዘንድ አስፈላጊ ነው ካሉ በኋላ፣ ብፁዕ አቡነ ማምበርት ፍቅር በሓቅ በሚል ርእስ ሥር ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ፓ. በነዲክቶስ 16ኛ የደረስዋት አዋዲት መልእክት ዋቢ በማድረግ ካለ እውነት እና ካለ እማኝነት እንዲሁም እውነትን ካለ ማፍቀር ሕሊና እና ማኅበራዊ ኃላፊነት አይኖርም፣ ለማህበራዊ ጉዳይ የሚደረገው ጥረት ባዶ እና የሥልጣን ሽኩቻ ሆኖ ይቀራል ብለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.