2009-10-02 14:37:06

የምሥራቅ አፍሪቃ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ኅብረት የጋራ ውሳኔ


የምሥራቅ አፍሪቃ አገሮች ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ማኅበር እ.ኤ.አ. ከጥቅምት 4 ቀን እስከ ጥቅምት 25 ቀን 2009 ዓ.ም. ሊካሄድ ተወስኖ ስላለው ሁለተኛው የአፍሪቃ ብፁዓን ጳጳሳት ሲኖዶስ ምክንያት አንድ RealAudioMP3 የጋራ መገልጫ ማውጣቱ ተገለጠ።

ይህ የኤርትራ ኢትዮጵያ ኬንያ ማላዊ ሱዳን ታንዛኒያ ኡጋንዳ እና ዛምቢያ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት የሚያቅፈው አሜሴአ በሚል አሕጽሮተ ቃል የሚታወቀው ማኅበር ባወጣው የጋራ መገልጫ መሠረት የዛሬ 15 ዓመት በፊት ከተካሄደው አንደኛው የአፍሪቃ ብፁዓን ጳጳሳት ሲኖዶስ ወዲህ በዚህች ከፍለ ዓለም የተከሰቱት አዳዲስ ፈታኝ ሁኔታዎች የተስፋ ምልክቶች በስፋት ተብራርቶበት እንደሚገኝ ፊደስ የዜና አገልግሎት በማስታወቅ፣ በአለማችን የተከሰተው የኤኮኖሚ ቀውስ በአፍሪቃ ኤኮኖሚ ማህበራዊ ጉዳይ ያስከተለው አቢይ ችግር በመጥቀስ እንዲሁም ሚሊዮኒም በሚል መጠሪያ ስም በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የተወጠነው እ.ኤ.አ. እስከ 2015 ዓ.ም. እንዲረጋገጥ የታቀደው ድኽነት የማጥፋታ እና የልማት እቅድ እግብር ላይ ይውላል ለማለት የዳጋች መሆኑ በመተንተን፣ እ.ኤ.አ. ከ 1990 ዓ.ም. ወዲህ ብዙ ብቃት በሌላቸው መሪዎች አማካኝነት የተከሰቱት ፖለቲካዊ ለዎጦች ያስገኘው የዴሞክራሲ ሥርዓት የኅብረ ፖለቲካ ሰልፎች መረጋገጥ እምብዛም አስተማማኝ እንዳልሆነ እና የተካሄዱት ሕዝባዊ ምርጫዎች ጭምር ሁከት እና መደናገር እንዲሁም አለ መግባባትን የታየበት እና ይኸንን ችግር ለማስወገድም የተከተሉት ሥልጣን የመከፋፈል ስልት የሕዝቦች ተስፋ እንዳጨለመም በመግለጥ በማኅበራዊ የአገልግሎት ዘርፎች የሚታየው ሙስና፣ ዓለም አቀፍ የተፈጥሮ እና የአካባቢ ብክላዎች በዚህ ክልል እያስከተለው ያለው የተፈጥሮ እና የአየር ንብረት ብከላ እና መዛባት ምክንያት ምሥራቅ አፍሪቃ ለተለያዩ ዘርፈ ብዙ ችግሮች መጋለጡ የብጹዓን ጳጳሳቱ መግለጫ እንዳመለከተውም ፊደስ አስታወቀ።

በነዚህ አገሮች ክልል የአቢያተ ክርስትያን መስፋፋት ብዙውን ጊዜ እምነትን ጠለቅ ለማድረግ በሚያግዝ እና ባህል በወንጌል መሰበክ እንዳለበት በሚያነቃቃ ስልት የማይሸኝ በመሆኑም ምክንያት ይህ ችግር እንዲወገድ የዚህ ክልል ብፁዓን ጳጳሳት የሚያደርጉት ጥረት የሚመሰገን ሲሆን የህዝቡ ችግር ተገን በማድረግ የተለያዩ የሻራ ሃይማኖቶች እየተስፋፉ መሆናቸውም ብፁዓን ጳጳሳት ያመለክታሉ።

በጠቅላላ እነዚህ ጉዳዮች መሠረት በማድረግ በምሥራቅ አፍሪካ አቢያተ ክርስትያን በኩላዊት ቤተ ክርስትያን የማህበራዊ ጉዳይ ትምህርት የተሸኘ መንፈሳዊነት እርቅ እና ፍትሕ ለማነቃቃት በሚያግዝ ስልት አማካኝነት የመጽሓፍ ቅዱስ ትምህርት ማስፋፋት አስፈላጊ መሆኑ በማመን ይኽ ሀሳብ ለሲኖዶስ እንደሚያቀርቡ እና ቤተሰብ የሚደገፍ የወጣቶች ሕንጸት ማነቃቃት እጅግ አስፈላጊ መሆኑ በፁዓን ጳጳሳት ባወጡት የጋራ ውሳኔ እንመለከቱ ፊደስ የዜና አገልግሎት አስታውቀዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.