2009-10-02 14:40:46

በሴቶች ላይ የሚፈጸመው አመጽ እንዲወገድ


ውጥረት በሚታይባቸው ክልሎች በሴቶች ላይ የሚፈጸመው የወሲብ አመጽ ጉዳይ በመከታተል የሚያጣራ የልኡካን ቡድን የሚመሩ እና የዚህ ቡድን የማጣራት ተልእኮ የሚያቀነባበሩ ልዩ ወኪል RealAudioMP3 መመረጡ ተገልጠዋል።

ግጭት እና ሁከት በሚታይባቸው ክልል በሴቶች ላይ የሚፈጸመው አመጽ በተለይ ደግሞ ገና ለአቅመ አዳም ያልደረሱ ሴቶች ላይ የሚፈጸመው የወሲብ አመጽ ጨርሶ እንዲወገድ ስለዚህ ጉዳይ በመደገፍ የሚካሄዱት ዘመቻዎችን የሚያነቃቃ እና ውጥረት ግጭት እና አለ መረጋገት በሚታይባቸው ክልሎች ያሉት መንግሥታት በሴቶች ላይ የሚፈጸመው አመጽ በማጣራት ተጠያቂዎች ለይቶ ለፍርድ ለማቅረብ እንዲተጉ የሚያነቃቃት ኃላፊነት መሆኑም ሚስና የዜና አገልግሎት በማስታወቅ ይህ ውሳኔ የተባበሩት መንግሥታት 15 የደህንነት እና የጸጥታ ምክር ቤት አባላት ፊት ተገኝተው የዚህ ምክር ቤት የወቅቱ ተረኛ ሊቀ መንበር የሆነውን የአገራቸው መንግሥት ወክለው የተሳተፉት የተባበሩት የአሜሪካ መንግሥታት ዋና ጻሓፊ ሂላሪ ክሊንቶን ያረቀቁት ንድፈ ሓሳብ በ 1888 ውሳኔ ዘንድ ተመልክቶ ይገኛል።








All the contents on this site are copyrighted ©.