2009-10-01 11:13:29

በየአፍሪቃ ጳጳሳት ሲኖዶስ ምክንያት ዕለተ አፍሪቃ ይከበራል ፡


የሮማ ከተማ መዘጋጃቤት ፊታችን ጥቅምት ወር አስራ ዘጠን ቀን፡ የአፍሪቃ ብጹዓን ጳጳሳት ሲኖዶስ ምክንያት በምድረግ አገሮች አቀፍ ዕለተ አፍሪቃ እንዲሆን መወሰኑ ተመልክተዋል።
ዕለቱ መነሻ በማድረግ ከቅትር በፊት የሃይማኖት የፖሊቲካ እና የግብረ ሰናይ ድርጅቶች ባለ ሙያዎች ያሳተፈ አፍሪቃ ትኩረት የሰጠ ልዩ ስብሰባ መዘጋጃ ቤቱ ውስጥ ይካሄዳል።

በዚሁ በርካታ የአፍሪቃ ጳጳሳት የሚስተፉት ስብሰባ የጳጳሳት ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ ብፁዕ አቡነ ኒኮላ ኤተሮቪች የቅድስት መንበር ቃል አቀባይ አባ ፈደሪኮ ሎምባርዲ የቅዱስ ኤጂድዮ መስራች ፕሮፈሶር አንድረአ ሪካርዲ ለስብሰባው ንግግር እንደሚያደርጉ ተመልክተዋል።

የሰነጋል መንግስት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ተድያነ ጋድዮ በተባበሩት መንግስስታት የእርሻ እና ምግብ ድርጅት ምክትል ዋና ጸሐፊ ሞዲቦ ትራኦረ የክብር እንግዶች መሆናቸውም ተመልክተዋል ።

ከቅትር በኃላም በኮንቺልያጽዮነ አውዲተርዩም የሙዚቃ የአፍሪቃ ሙዚቃ እና ባህሎች ትዕይንት እንደሚታዩ ተገልጸዋል ።

ስብሰባውም ሆነ የአፍሪቃ የሙዚቃ እና ባህል ትዕይንቱ በየጳጳሳት ሲኖዶስ ጉባኤ በሮማ ከተማ መዘጋጃ ቤት በየሮማ ቅዱስ የቅዱስ ኤጂድዮ ማኅበረሰብ እና ራድዮ ቫቲካን የተዘጋጀ እና የተቀናበረ መሆኑ ይታወቃል ።








All the contents on this site are copyrighted ©.