2009-09-30 13:40:37

የርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት አስተምህሮ


ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ዛሬ ረፋድ አጠቃላይ ሳምንታዊው የዕለተ ረቡዕ ጉባኤ አስተምህሮ ማቅረባቸው ሲመለከት፣ ቅዱስነታቸው ዛሬ ባጭሩ ለእንግሊዝኛ ተናጋሪዎች ያሰሙት መልእክት RealAudioMP3 እንደሚከተለው ነው፦

ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ቀናት ወደ ቸክ ረፓብሊክ ያደረኩት ሐዋርያዊ ጉዞ ሁለቱም ማለት መንፈሳዊ እና ሐዋርያዊ ግብረ ተልእኮ ዓላማ የነበረው ነው።

መንፈሳዊ ንግደት የሚሆንበት ምክንያት የቸክ ምድር በመንፈሳዊና ቅዱስ ሕይወታቸው ለክርስቶስ የመሰከሩ ብዙ ቅዱሳን ያለፉበት እና የኖሩበት በመሆኑ፣ ሓዋርያዊ ግብረ ተልእኮ የሚሆነው ደግሞ የኤውሮጳ አህጉር በወቅቱ ክርስቶስን ከመከተል የሚገኝ ደስታ እና ተስፋ እንደገና መገንዘብና ማወቅ ስለሚያስፈልጋት ነው።








All the contents on this site are copyrighted ©.