2009-09-30 13:48:29

ኬጻና የሚል መጠሪያ የተሰጠው ዝናብ አዘል ኃይለኛው አውሎ ነፋስ


ፊሊፒንስ ያጠቃው ዝናብ አዘል ኃይለኛው ዓውሎ ነፋስ አቅታጫውን በማዞር ቬትናምን ላኦስን እና ታይላንድን እያጠቃ መሆኑ ተገልጠ። በፊሊፒስን በዚህ የተፈጥሮ አደጋ ሳቢያ 240 ሰዎች ሕይወታቸው እንዳጡ ሲነገር፣ RealAudioMP3 በቨትናም 23 ሰዎች ለሞት እና ሌሎች 170 ሺሕ የሚገመተው ሕዝብ ቤቱን እና ንብረቱን ጥሎ ለመፈናቀል አደጋ ማጋለጡ ሲነገር፣ ለተጎዳው ህዝብ ካሪታስ በሚል መጠሪያ የሚታወቀው የካቶሊክ ቤተ ክርስትያን የተራድኦ ማኅበር ካናዳ በሚገኘው ቅርንጫፉ አማካኝነት አቢይ የሰብአዊ መንፈሳዊ እና ቁሳዊ ድጋፍ በማቅረብ ላይ መሆኑ ሲነገር፣ የዚህ የካናዳው የካሪታስ ማኅበር አባል ጁሊዮ ብሩነሊ ከቫቲካን ረድዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ በፊሊፒንስ በጎርፍ መጥለቅለቅ አደጋ ለተጠቃው በብዙ ሺሕ ለሚገመተው ሕዝብ ተቀዳሚ እና መሠረታዊ ድጋፍ እየቀረበ መሆኑ ጠቅሰው፣ ለሞት እና ለመፈናቀል አደጋ ከተጋለጠው ሕዝብ አንዳንዶች ገና በመፈለግ ላይ ናቸው ብለው፣ በጠቅላላ ግማሽ ሚሊዮን የሚገመት ሕዝብ ባደጋው በመጠቃቱ ምክንያት በዚህ ድጋፍ በማቅረብ ርብርቦሽ የዓለም አቀፍ ማህበረሰብ ትብብር እና ድጋፍ ወሳኝ ነው ብለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.