2009-09-30 13:46:02

በማኅበራዊው ሕይወት ማእክል እንድትሆን አደረገ


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲቶስ 16 እ.ኤ.አ. ከ ጥቅምት 26 ቀን እስከ 28 ቀን 2009 ዓ.ም. በሬፓብሊክ ቸክ ያካሄዱት 13ኛው ዓለም አቀፍ ሓዋርያዊ ጉብኝት፣ ኃይማኖትን ችላ ባይ ባህል እያንሰራፋ ባለበት ወቅት RealAudioMP3 የዚህች አገር ካቶሊክ ቤተ ክርስትያን በማኅበራዊው ሕይወት ማእክል እንድትሆን ማድረጉ የርእሰ ከተማ ፕራግ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ ካርዲናል ሚሎስላቭ ቭልክ ከቫቲካን ሬድዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ በማብራራት፣ የር.ሊ.ጳ. ሓዋርያዊ ጉብኝት በፊት በአገሪቱ የመገናኛ ብዙኃን ሬፓብሊክ ቸክ የኢአማኒነት አመለካከት የተስፋፋባት እንደሆነች ነበር የሚነገረው ሆኖም ግን ይህ ተስፋ ያነገበው የቅዱስ አብታችን ሓዋርያዊ ጉብኝት በእውነቱ እምነትን የቀሰቀሰ ኢአማኒነትን በጥያቄ ውስጥ ያስገባ አቢይ ጸጋ ነበር ብለዋል።

የአገሪቱ ማኅበራዊ እና ቤተ ክርስትያናዊ ገጽታዋን ያጎላው ቅዱስ ጠባቂ ሰማእት ቨንቸስላው ሰማዕትነት የተቀበለበት 200ኛው ዓመት በመጥቀስ የሰጡት አስተምህሮ አቢይ እና ልዩ ትርጉም ያለው የቼክ ረፓብሊክ ሕዝብ መንፈሳዊነትን በመዳሰስ ዛሬ ሕያው እንዲሆን የጠራ ነበር በማለት፣ ያች አነስተኛ እና አናሳው የቼክ ሬፓብሊክ ሕዝብ የምትወክል በአገሪቱ የምትገኘው የካቶሊክ ቤተ ክርስትያን፣ ብቸዋ እንዳልሆነች እና የእንተ ላእለ ኵሉ ካቶሊክ ቤተ ክርስትያን ክፍል መሆኗ የተመሰከረበት እና በዚህ ዓለም አቀፋዊ የግብረ ገብ ዓቢይ ሥልጥን ያላቸው በርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሥር መሆኗ በመመስከሩም፣ በማኅበራዊው ሕይወት እና በኅብረተሰቡም ዘንድ ተገቢው ቦታ ያሰጣት እና አቋሟንም ጭምር ያጎላ ነው ብለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.