2009-09-30 13:49:49

ለቅዱስ ፍራንቸስኮስ ዘ አሲዚ ክብር


እፊታችን ቅዳሜ እና እሁድን በኢጣሊያ አሲዚ ከተማ የተለያዩ ሃይማኖት መንፈሳዊ መሪዎች የከተማይቱ ምክር ቤት ተጠሪዎች እና የብሄራዊው መንግሥት ተወካዮች የሚሳተፉበት ስለ ቅዱስ ፍራንቸስኮች ክብር መንፈሳዊ ባህላዊ መርሃ RealAudioMP3 ግብሮች እንደሚከናወኑ ሲር የዜና አገልግሎት አስታወቀ።

የዜናው አገልግሎት እንዳሚያመለክተውም በዚህ የሁለት ቀን በዓል ለመሳተፍ ከኢጣሊያ እና ከተለያዩ አገሮች የተወጣጡ መንፍሳዊ ነጋድያን አሲዚ ከተማ እየገቡ መሆናቸው ሲታወቅ፣ በጠቅላላ የሚከናወነው መንፈሳዊው እና ባህላዊው መርሃ ግብር የቅዱስ ፍራንቸስኮስ ስበአዊ እና መንፈሳዊ ሂደቶች የሚዳስስ እንደሚሆን ሲገለጥ፣ በዓሉ በላቲን ሥርዓት ጥቅምት 4 ቀን ቅዱስ ፍራንቸስኮስ የሚዘከርበት ዕለት የፖተንዛ ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ አቡነ አጎስቲኖ ሱበርቦ በሚመሩት መሥዋዕተ ቅዳሴ ይፈጸማል። ቅዱስ ፍራንቸስኮስ የኢጣሊያ ጠባቂ ቅዱስ በመሆኑም ምክንያት በብሔራዊ አቀፍ ደረጃ ታስቦ እንደሚውልም ሲር የዜና አገልግሎት አስታወቀ።








All the contents on this site are copyrighted ©.