2009-09-30 16:24:32

.ለሐቅ ክፍት መሆን ይገባል፡


ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ በቸክ ረፓብሊክ አገሮች አቀፍ አስራ ሶስተኛ ሐዋርያዊ ጉብኝት ፈጽመው ከትናንትና ወድያ ወደ ካስተል ጋንደልፎ ሐዋርያዊ መንበራቸው መመለስቻው የሚታወቅ ነው ።

ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ ከቸክ ረፓብሊክ ርእሰ ከተማ ፕራግ አውሮፕላን ማረፍያ ሲነሱ አሸኛነት ለዳረዱላቸው የቸክ ረፓብሊክ የሃይማኖት እና የመንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናት ንግግር ማድረጋቸው የሚታወስ ነው ።

ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ ከቸክ ረፓብሊክ አውሮፕላን ማረፍያ ሲነሱ መለኮታዊ ቁንጅና ለዓለም እንዲያንጸባርቅ ለሐቅ ክፍት ትሆኑ ዘንድ እመኛለሁ ብለዋል ።

ቸክ ረፓብሊክ የተባረከች ሃገር ናት ምክንያቱም አንጋፋዎች ሚስዮናውያን እና ሰማዕታት ያበቀለች ቅድስቲ የክርስትያን እሴቶች አቀፍ ሀገር ናት ሲሉ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ ቸክ ረፓብሊክን አወድሰዋል ።

ቸክ ረፓብሊክ በኮሚኒስት አገዛዝ ስር በነበረችበት ግዜ የተገደለች ቅድስት አኘሰ ዘ ቦኤሚያ እና በስታራ ቦስላቭ ማዕትት የሆነ ቅዱስ ቨንሰስላው አስታውሰዋል ።

ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ ከሀገርቱ ከሶስት የክርስትያን ማኅበረሰቦች ተውካዮች ያደረጉት ውይይት ዘክረው በየክርስትያኖች መካከል ዘውትር ውይይት ማካሄድ ተኪ የሌለው አስፈላጊነት እንዳለው ገልጸዋል።

እንዲሁም ከቸክ ረፓብሊክ ወጣቶች ያካሄዱት ግንኙነት አስታውሰው ፡ ወጣቶቹ በሀገሪቱ የክርስትና እሴቶች ተመርኩሰው ሀገሪቱ ለማነጽ ዓቢይ ተስፋ እንዳላቸው አመልክተዋል።

ፈላስፋ ፍርንስ ካፍካ ጠቅሰው የፍጥረት መልካምነት የያዘ ሰው ከቶ አያርጅም ብለዋል።

ዓይናችን የእግዚአብሔር ፍጥረት ፡ አእምሮአችን ደግሞ ሐቅነቱን ለማየት ክፍት ከሆኑ ወጣቶች ሆነን ለመቅረት እና መኮታዊ ቆንጆነት ለማነጥ ለመጪው ትውልድ መልካም እና የተባረከ ባህል ለመተው ተስፋ አለን ማለት ነው ሲሉ ቅዱስ አባታችን በነዲክቶስ አመልክተዋል ።

በመጨረሻ በቸክ ቋንቃ “ አት ፕራዘስክ ጀዙላትኮ ፡ እግዝአብሔር ቸክ ረፓብልክን ይባራክ” ብለዋል ።

የቸክ ረፓብሊክ መንግስት ፕረሲዳንት ክላውስ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ በቸክ ረፓብሊክ ያካሄዱት ሐዋርያዊ ጉብኝት አምስግነው ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ለሀገሪቱ ህዝብ አዲስ ተስፋ መስጠታቸው የቸሩት አባታዊ ምክር ገቢራዊ ለማድረግ እንጥራለን በማለት ገልጸዋል።

ፕረሲዳንት ክላውስ አያይዘው የርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት አቋም በፖሊቲካ ረገድ ሲታይ በሁሉም ወይም በአብዛኞዎቹ ትክክለኛ እና ተቀባይነት ያለው ነው ካሉ በኃላ የቸክ ረፓብሊክ ህዝብ መሠረታዊ የስልጣኔ እና ክርስትና መርሆች እንዲከተል ያሰሙት ንግግር ተቀባይነት ያለው ስለ ሆነ ይህንኑ ገቢራዊ እንዲሆን እኔ ራሴ አርአያ ለመሆን እጥራለሁኝ ብለዋል።

ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ የቸክ ረፓብሊክ ሐዋርያዊ ጉብኝት ስኬታማ መኖሩ እና የሀገሪቱ ህዝብም በዚሁ ጉብኝት በእጅጉ መደሰቱ የቸክ ረፓብሊክ እና የውጭ መገናኛ ብዙኀን ዘግበዋል ።



!!!!!!!!!!!!!!!








All the contents on this site are copyrighted ©.