2009-09-28 14:47:10

አባ ሎምባርዲ፣ ተስፋን ማእከል ያደረገ ሓዋርያዊ ጉብኝት


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ በሬፓብሊክ ቼክ እያከናወኑት ያለው ሓዋርያዊ ጉብኝት እውነት እምነት ነጻነት በተለይ ደግሞ ተስፋ እያስተጋባ፣ የዚህች አገር ምእመናን እምነታቸውን በመኖር እንዲገልጡዋቸውም ዘንድ RealAudioMP3 እያነቃቃ መሆኑ ቀዱስነታቸው ትላትና ጧት በብርኖ መሥዋዕተ ቅዳሴ በማቅረብ ካሰሙት ስብከት ለመረዳት እንደሚቻል የቅድስት መንበር የዜና እና የማኅተም ክፍል ተጠሪ ኣባ ፈደሪኮ ሎምባርዲ አስታውቀዋል።

የቅዱስ አብታችን ር.ሊ.ጳ. የሬፓብሊክ ቼክ ሓዋርያዊ ጉብኝት ማእከል ተስፋ የሚለው ቃል መሆኑ እና፣ ቅዱስነታቸው በተከታትታይ በተለያዩ ወቅቶች እና በተለይ ደግሞ በተስፋ ድነናል በሚል ርእሥ ሥር ከደረስዋት ከመጀመሪያቱ ዓዋዲት ምልእክት እንደምንረዳውም ተስፋ የሚል ቃል በሓዋርያዊ መሪነታቸው ዘንድ ዓቢይ ሥፍራ እንዳለው ለማረጋገጥ አያዳግትም፣ ስለዚህ ሓዋርያዊ ጉብኝቱ ተስፋ ማእከል ያደረገ ነው፣ እውነተኛው ተስፋ በየእለቱ ብቅ ከሚሉት ተናንሽ ተስፋዎች ለየት ያለ አቢይ የማይሞት በየእለቱ ፈተና የማይሸነፍ ልቆ የመሄድ አቅም ያለው የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ትንሳኤ ያረጋገጠውን የሚመከሰክረው ነው ብለዋል።

ነጻነት በእውነት እና በኃላፊነት የተመራ በማድረግ ሕዝቦች ከመደናገር ማላቀቅ ወሳኝ መሆኑ የመሰከረ ኤውሮጳዊ አንድነት በባህል በመንፈስ የጸና የጋራ እሴቶች የሚያንጸባርቅ እንጂ ክፍለ ዓለማዊነት መለያ ያለው እንዳልሆነ የሚመሰክር ሓዋርያዊ ጉብኝት ነው ብለዋል።

እሁድ ቅዱስ አባታችን በመሩት መስዋዕተ ቀዳሴ 100 ሺሕ ምእመናን መሳተፉ ኣባ ሎምባርዲ ገልጠው፣ በቅዳሴ የታየው ሱታፌ በርግጥ ሬፓብሊክ ቼክ ለሁለት ዘመን የዘለቀው እምነትን እና ሃይማኖትን ችላ በሚል ባህል የተጠቃች ብትሆንም ቅሉ የክርስትያን ምእመናን መንፈስ በዚያኑ ልክ ምንኛ ሕይወት እንዳለው እና መንፈሱም ሌላውን እየነካ መሆኑ የጎላበት አጋጣሚ ነበር በማለት፣ ከዚህ አንጻር የክልሉ ክርስትያን ማኅብረሰብ ያለው ኃላፊነት አቢይ መሆኑ ለመረዳት ይቻላል ሲሉ የሰጡትን ቃለ ምልልስ ደምድመዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.