2009-09-28 14:46:00

ለቤተ ክርስትያን ሬፓብሊክ ቼክ ልዩ አዲስ ኃይል


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ በመካከለኛው ኤውሮጳ ክልል የምትገኘው ሬፓብሊክ ቼክ እያካሄዱት ያለው ሓዋርያዊ ጉብኝት የእምነትን ምክንያት እና ተስፋን የሚያነቃቃ ለአገሪቱ ቤተ ክርስትያን አዲስ ኃይል RealAudioMP3 የሚያጎናጽፍ ነው ሲሉ፣ በሬፓብሊክ ቼክ የቅድስት መንበር ወኪል ብፁዕ አቡነ ዲየጎ ካውሰሮ ስለ ሓዋርያዊው ጉብኝት በማስመልከት ከቫቲካን ረድዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ በማብራራት፣ ሐዋርያዊው ጉብኝት የአማኞች ብቻ ሳይሆን የኢአማንይና ትኵረት ጭምር የሳበ መሆኑ ጠቅሰው፣ ካቶሊክ ምእመናን ይህ ለክልሉ ካቶሊክ ቤተ ክርስትያን ልዩ እና አዲስ ኃይል የሚያሰጠው የቅድስ አብታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ሓዋርያዊ ጉብኝት በጉጉት ይጠባበቅ ነበር ብለዋል።

የሬፓብሊክ ቼክ ክርስትያን ማኅበርሰብ በጭቆና እና በስደት ለብዙ ስቃይ ተጋልጦ እንደነበር ዘክረው ነገር ግን እራሱን ቀና በማድረግ እምነቱን ከመመስከር አልተቆጠበም ካሉ በኋላ፣ የክልሉ ካቶሊክ ክርስትያን ማኅበርሰብ ከአገሪቱ ህዝብ ብዛት አንጻር ሲታይ 30 በመቶ የሚሸፍን መሆኑ ጠቅሰው፣ በወጣት ክርስትያን ምእመናን እና በወጣት ካህናት ኃይል የተሞላች ነች ብለዋል።

የቼክ ሬፓብሊክ ቤተ ክርስትያን ለ 200 ዓመት የሚገመት ማለትም በመጀመሪያ ከፈረንሳ አብዮት ተምሳይነት ባለው እምነትን እና ሃይማኖትን ችላ በሚል ባህል ቀጥላም የኮሙኒዝም ሥርዓት ምንጭ ባደረገው እምነትን እና ሃይማኖትን ችላ በሚል ባህል ተጠቅታ ሃይማኖት አደዛዥ እጸዋት እንደሚያስከትለው ሱስ የሚታይበት ዘመን የፈተናት ነች ብለው፣ በጠቅላላ ለ 200 የጸረ ካቶሊክ አመለካከት እና ተግባር ጎልቶ የታየባት አገር ነች ብለዋል።

የአገሪቱ ፖሊቲካ ከሁሉም ሃይማኖት ነጻ ቢሆንም ቅሉ የፖለቲካ አካላት እምነት የሌላቸው ነገር ግን አንድ የላቀ ኃይል አለ የሚል ይህ ደግሞ ባህርያዊ ሃይማኖት እንደሆነ እና በያንዳንዱ ዘንድ ያለ ስሜት ሆኖ በዚህ የስሜት ባህርያዊ ሃይማኖት የሚያምኑ ሆነው የዚህ የላቀው ኃይል ማንነት የእያንዳንዱ ሰው የአእምሮ ነጻነት ይወስነዋል በሚለው ባህል የሚመሩ ቢሆንም ቅሉ፣ የክልሉ ካቶሊክ ቤተ ክርስትያን ምእመናን እምነት ሃይማኖትን ችላ በሚል ባህል የተጨቆነ እና ለስደት በዳረገው እሳት የተፈተነ በመሆኑ፣ በብቀላ ሳይሆን ለር.ሊ.ጳ. እና ለብፁዓን አቡናት ባላቸው ፍቅር እና ታዛዥነት አማካንኝነት ወንጌልን በመኖር ምላሽ የሚሰጥ ነው ብለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.