2009-09-25 14:10:08

ፍቅር በሐቅ፣ ለተሟላ እድገት መሠረት


ቅዱስ አብታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16 ፍቅር በሓቅ በሚል ርእስ ሥር የደረስዋት ዓዋዲት መልእክት ማእከል ያደረገ ቶከይቪል አክቶን የጥናት ማእከል እና የኢጣሊያ የባህል ጉዳይ ሚኒስትር በመተባበር ያነቃቁት ዓውደ ጥናት ትላንትና RealAudioMP3 በቅድስት ማርታ የጉባኤ አዳራሽ መከናወኑ ተገለጠ።

በጳጳሳዊ ላተራነሰ መንበረ ጥበብ እንዲሁም በሉዊስ መንበረ ጥበብ መምህር እና የቶከይቪል አክቶን የጥናት ማእከል ሊቀ መንበር ፕሮፈሶር ፍላቪዮ ፈሊቸ፣ አውደ ጥናቱ አጋጣሚ በማድረግ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ ፍቅር በሓቅ የተሰኘቸው የቅዱስ አብታችን ዓዋዲት መልእክት በአለማችን ተከስቶ ያለው የኤኮኖሚው መቃወስ እና ስለ ጉዳዩ በብሔራዊ አቀፍም ይሁን በዓለም አቀፍ ደረጃ በተለይ ደግሞ በኢንዳስትሪ የበለጸጉት 20 አገሮች እያካሄዱት ላለው ጥረት ዋስትና ነች በማለት፣ ቅዱስ አባታችን የካቶሊክ ቤተ ክርስትያን ማህበራዊ ትምህርት ጉዳይ በሙላት በማካተት የአለማችን ማህበራዊ ኤኮኖሚያዊ ፖለቲካዊ ሰብአዊ ቀውስ ጠለቅ በማድረግ በማስተንተን በቤተ ክርስትያን ታሪክ ያለፉት ርእሳነ ሊቃነ ጳጳሳት ካለ መታከት የዳሰሱት እና መሪ ቃል የሰጡባቸውን ዓዋዲ መልእክቶችንም በማጥናት ወቅታዊው ዓለም በመቃኘት ያቀረቡዋት ዓዋዲት መልእክት፣ የሰውል ልጅ የተሟላው እንድገት ማረጋገጥ ስነ ምግባር በሁሉም ዘርፍ ማካተት ወሳኝ መሆኑ ጥሪ የምታቀርብ ብቻ ሳትሆን ለማክበሩም ለመከተሉም ምን መደረግ እንዳለበት መሪ ቃል የቀረበባት ነች፣ ስለዚህ የሰው ልጅ ሙሉአዊ እድገት ያላነጣጠረ ማንኛውም ዓይነት ጥረት እግብ እንደማይደርስ አብጠርጥራ የምታስረዳ መሆኗ ትላትና የተካሄደው አውደ ጥናት ያረጋግጣል ብለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.