2009-09-25 14:06:46

የአፍሪካ ወጣቶች ለሰላም ባህል ማሠልጠን


የኮንጎ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ሊቀ መንበር የሹምቤ ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ ኣቡነ ኒኮላስ ድጆሞ እ.ኤ.አ. ከጥቅምት 4 ቀን እስከ ጥቅምት 25 ቀን 2009 ዓ.ም. እዚህ በቫቲካን ሊካሄድ ተወስኖ ስላለው የአፍሪካ ሁለተኛው ሲኖዶስ RealAudioMP3 በማስመልከት ከቫቲካን ሬዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ ይህ በ 1994 ዓ.ም. ከተካሄደው አንደኛው የአፍሪካ ብፁዓን ጳጳሳት ሲኖዶስ ቀጥሎ ልክ በ 15ኛው ዓመት የሚከናወነው ሁለተኛ ሲኖዶስ መሆኑ በማስታወስ፣ የአፍሪካ ካቶሊክ ቤተ ክርስትያን ልኡካነ ወንጌል የተለያዩ የመንፈሳዊ ማህበር አባላት የካቶሊክ ቤተ ክርስትያን ትምህርት ቤቶች ተቋሞች እና መናብርተ ጥበብ በአፍሪካ ሰላም ፍትህ እርቅ እኵልነት የሰብአዊ መብት እና ፈቃድ መረጋገጥ የመሳሰሉት አበይት እና ለማህበራዊ ኑሮ መሠረት የሆኑት ዕሴቶችን በማነቃቃት ረገድ አቢይ አገልግሎት እየሰጡ መሆናቸውም ገልጠው፣ በተለይ በአፍሪካ የሚገኙት የካቶሊክ ቤተ ክርስትያን የመገናኛ ብዙሃን የተጠቀሱት ዕሴቶችን በተለያየ ዘርፍ በማነቃቃት የቤተ ክርስትያን የማህበራዊ ጉዳት ትምህርት መሠረት በማድረግ የሁሉም ዕሴቶች ማእከል የሰው ልጅ መሆኑ ጠለቅ ባለ መልኩ አስተምህሮ ያቅርባሉ ብለዋል።

በመጨረሻም፣ ቅዱስ አብታችን ር.ሊ.ፓ. በነዲክቶስ 16ኛ ኢየሱስ ናዝራዊ በሚል ርእስ ሥር በጻፉት መጽሓፍ እንደሚያስነብቡት፣ ህዝብ ብቻ ሳይሆን ባህል ጭምር ሊስከበክ ይገባውል። ስለዚህ በአፍሪካ የሚከናወነው ስብከተ ወንጌል ይኸንን ዓላማ ያካተተ መሆን እንዳለበት ገልጠው፣ ሁለተኛው ያፍሪካ ሲኖዶስ አፍሪካ የሰላም መሬት እንድትሆን ወጣቱ ትውልድ ለሰላም ባህል ማሠልጠን ወሳኝ መሆኑ ከማሳሰብ እና መሪ ሃሳብ ከመንደፍ ወደ ኋላ እንደማይል ነው በማለት ቃለ ምልልሱን ደምድመዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.