2009-09-23 13:40:09

የዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ ትብብር ሰላም ለማረጋገጥ ወሳኝ ነው


የሱዳን ደህንነት እና ጸጥታ እንዲረጋገጥ የአገሪቱ መንግሥት የሚከተለው ውሳኔ አጥጋቢ እንዳልሆነ የሚያሳስብ የቶምቡራ እና ያምቢዮ ሰበካ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ኤድዋርድ ሂቦሮ ኩሳላ ያነቃቁት የጸረ አመጽ ጥሪ የሚያተጋባ 20 ሺሕ ክርስትያኖች RealAudioMP3 የተሳተፉበት የሁለት ኪሎ ሜትር መንፈሳዊ የእግር ጉዞ መከናወኑ ዜኒት የዜና አገልግሎት አስታወቀ።

በሱዳን የሚፈጸመው ዓመጽ፣ ጠለፋ እና ሥውር የቅትለት ደባ ጨርሶ እንዲወገድ የዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት እና ፈቃድ አስከባሪ ተሳትፎ እጅግ ወሳኝ ነው ሲሉ ብፁዕ አቡነ ሂቦሮ ኩሳላ ማሳሰባቸው የዜና አገልግሎት በመጠቆም፣ ባለፈው ወር በኤዞ ክልል በምትገኘው የሰላም ንግሥት ቤተ ክርስትያን መሣሪያ የታጠቁ ሰዎች ዘልቀው በመግባት 17 ክርስትያን መእመናን መጥለፋቸው እና ከነዚህ ከተጠለፉት ወጣቶች ውስጥ ሲገደል፣ 3 በማምለጥ ወደ ቤታቸው መመለሳቸው የዜናው ምንጩ በመግለጥ፣ ሌሎች 13 የት እንዳሉ በውኑ የታወቀ ነገር አለ መኖሩ የዜናው አገልግሎት ከክልሉ ያገኘው መረጃ በመጥቀስ አስታውቀዋል።

የዚህ አይነት የማህበራዊ ኑሮ ጸጥታ እና ደህንነትን የሚያናጋው አሰቃቂው ድርጊት እንዲገታ የዓለም አቀፍ ማኅበርሰብ ትብብር እና ድጋፍ አስፈላጊ መሆኑ ብፁዕ አቡነ ኤድዎርድ ሂብሮ ኩሳላ መግለጣቸው ዜኒት የዜና አገልግሎት አስታውቀዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.