2009-09-23 17:00:46

የመካከለኛው ምስራቅ የመጀመርያ ሲኖዶስ አዘጋጅ ምክር ቤት :


ፊታችን ጥቅምት ወር ውስጥ የመካከለኛው ምስራቅ የመጀመርያ ሲኖዶስ አዘጋጅምክር ቤት እዚህ ቫቲካን ውስጥ እንደሚሰበሰብ የጳጳሳት ሲኖዶስ ጽሕፈት ቤት ያወጣው መግለጫ አስታውቀዋል።

በዚሁ መግለጫ መሠረት የመካከለኛው ምስራቅ የመጀመርያ ሲኖዶስ ፊታችን ዓመት 20010 እኤአ ከጥቅምት አስር እስከ ሃያ አራት ቀን እንዲከናወን በእቅድ ተይዘዋል ።

የዚሁ በዓይነቱ ለመጀመርያ ግዜ የሚከናወነው የመካከለኛው ምስራቅ የጳጳሳት ሲኖዶስ በመካከለኛውምስራቅ ካቶሊካዊት ቤተክርስትያን አንድነት እና ምስክርነት በተሰየመ ርእስ እንደሚጅመር መግለጫው ለጥቆ ገልጸዋል።

ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ ባለፈው ቅዳሜ ከየመካከለኛው ምስራቅ ፓትርያርካት ጋር መገናኘታቸው እና ሲኖዶሱ ትኩረት በሰጡ ርእሰ ጉዳዮች መወያየታቸው የሚታወስ ነው።

በቅድስት መንበር የጳጳሳት ሲኖዶስ ዋና ጽሐፊ ብፁዕ አቡነ ኒኮላ ኤተሮቪች እንዳመለከቱት የመካከለኛ ምስራቅ የጳጳሳት ሲኖዶስ የክልሉ ሃገራት ወቅታዊ ሁኔታ አንድ በአንድ ተመልክቶ ሰላም የሚነግስበት ሁኔታ ያፈላልጋል።

የካቶሊካውያን ጳጳሳት ሲኖዶስ ዋና ጽሐፊ ብፁዕ አቡነ ኒኮላ ኤተሮቪች እንደገለጹት ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ የመካከለኛው ምስራቅ የሰላም ሁኔታ ያሳስባቸዋል።

በፓለስጢና የኢየሩሳሌም የላቲን ፓትርያርክ ብፁዕ አቡነ ፎዓድ ጥዋል በመካከለኛው ምስራቅ የሚኖሩ ክርስትያኖች ኢስላም እና ይሁዲ ማኅበረሰቦች በሰላም እጦት ምክንያት እንደሚሰቃዩ ጠቅሰው የክልሉ ጳጳሳት ሲኖዶስ መካሄድ እጅግ መልካም ነው ብለዋታል።

በየኢየሩሳሌም የላቲን ሥርዓት ፓትርያርክ ፎዓድ ጥዋል እንዳመለከቱት ሲኖዶሱ አስፈላጊ እና ጠቃሚ የሚሆንበት ምክንያት በመጀመርያ በአየቃላይ የክርስትያን አብያተክርስትያናት ተጠሪዎች መካከለኛው ምስራቅ በተመለከተ የጋራ አቋም ይዙና ከዚህ ተነስተው ከየኢላም እና ይህዲ ማኅበረሰቦች ተወካዮች ለመነጋገር ስለሚችሉ።

ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ባለፈው ግንቦት ወርበ ዮርዳኖስ ፓለስጢና እና እስራኤል ያደረጉት ሐዋርያዊ ጉብኝት ጠቃሚ እና ለሰላም አጋጅ መኖሩ ያመለከቱት ፓትርያርክ ፎዓድ ጥዋል የመካከለኛው ምስራቅ ቤተክርስትያን ትብብር እና የሰላም ውይይት እንደሚያስፈልጋት ገልጠዋል።

የመካከለኛው ምስራቅ ህዝብ እንደ ሌሎች የዓለም ሀገራት የተለመደ ሕይወት ለማካሄድ ዕድል አጥቶ በፍርሃት እንደሚኖር ያመለከትቱት ፓትርያርክ ፎዓድ ጥዋል ይህ ሁሉ መወገድ አለበት መግለጫ መስጠታቸው ተመልክተዋል ።

በመካከለኛው ምስራቅ በተለይ በፓለስጢና ዘወትር ግጭት ስለ ሚከሰት ህዝብ ሀገሩ እና ንብረቱ ጥሎ ለስደት እየተዳረገ መሆኑም ፓትርያርኩ አስታውቅዋል ።








All the contents on this site are copyrighted ©.