2009-09-23 13:37:48

ሚለኒዩም የልማት እቅድ እግብ ለማድረስ


ፓክስ ክሪስቲ ሰላመ ክርስቶስ የተሰኘው ሰላም የሚያነቃቃው ዓለም አቀፍ ማኅበር በተባበሩት መንግሥታት ደረጃ እ.ፈ.አ. በ 2000 ዓ.ም. ሚለኒዮም በሚል መጠሪያ በአለማችን የሚታየው ድኽነት በግማሽ እንዲጎድል የወጠነው የልማት እቅድ RealAudioMP3 ሂደት እና በአለማችን የሚታየው የጦር መሣሪያ ንግድ በማነጻጸር ጥናታዊ ሰነድ ማቅረቡ ተረጋገጠ።

ሰነዱ እንደሚያመለክተውም የሚለኒዩም የልማት እቅድ እግብ ለማድረስ በተመደበው የወጪ እቅድ ተጨማሪ 35 ሚሊያርድ ዶላር ማከል እንደሚያስፈልግ ይህ ደግሞ ባለፈው ዓመት በአለማችን ለጦር መሣሪያ ግዥ ከፈሰሰው ጠቅላላ የገንዘብ ሃብት ውስጥ 4%ኛውን የሚሸፍነውን ወጪ የሚመለከት መሆኑ ለማወቅ ተችለዋል።

የገንዘብ ሃብት እጥረት አማካኝነት በተባበሩት መንግሥታት የተወጠነው እና እ.ኤ.አ. እስከ 2015 ዓ.ም ሊደረስ ታስቦ ያለው የልማት እቅድ ተጨባጭ ይሆናል ለማለት በጣም እንደሚያዳግት የፓክስ ክርስቲ ማኅበር ሰነድ በማመልከት፣ ለልማት እና ለጦር መሣሪያ ምርት አቅርቦት እና ግዥ የሚፈሰው የገንዘብ ወጪ ቢነጻጸር በእውነቱ የሚያሳፍር ብቻ ሳይሆን ለጦር መሣሪያ ግዥ የሚፈሰው የገንዘብ ሃብት ለልማት እቅድ ቢውል የልማቱ እቅድ በጥቂት ዓመታት ውስጥ እግብር ላይ እንደሚውል ያመለከተው ሰነድ፣ የሚለኒዮም የልማት እቅድ እግብር ላይ ለማዋል ሁሉም አገሮች በተለይ ደግሞ የበለጸጉት አገሮች ከምጣኔ ሃብታቸው 0.7% ይመድቡ ዘንድ የተደረሰው ስምምነት በስዊድን በሉሰምበር በኖርወይ በዴንማርክ እና በስዊዘርላንድ ብቻ መከበሩ ሰነዱ በማብራራት የተባበሩት ያሜሪካ መንግሥታት ለወታደራዊ ጉዳይ ከሚውለው ጠቅላላ ወጪ 10% ብቻ የሚሊዮነም እቅድ እግብር ላይ ለማዋል እንደሚያስችል የፓክስ ክሪስቲ ሰነድ ይጠቁማል።








All the contents on this site are copyrighted ©.