2009-09-21 13:28:31

የመን


በየመን ሰሜናዊ ክልል በምትገኘው በሳአዳ ክፍለ ሃገር የአገሪቱ መደበኛ ሠራዊት 140 የሺዒቶች አማጽያን ኃይል አባላት ለሞት መዳረጋቸው ተገልጠዋል። አንዳንድ የዓይን ምስክሮች እንደሚሉትም RealAudioMP3 ከሆነ እ.ኤ.አ. መስከረም 11 ቀን 2009 ዓ.ም. ግጭቱ አንድ ብሎ ከተጀመረበት ዕለት ወዲህ ከትላትና በስትያ የተካሄደው በጣም ኃይለኛ እና መጠነ ሰፊ እንደነበር ታውቀዋል።

ጦርነቱ እተካሄደበት ባለው ክልል ለሚኖረው ሰላማዊ ሕዝብ አስፈላጊው የሰብአዊ እርዳታ ለማቅርብ እንዲያመች የአገሪቱ መንግሥት የራማዳን ወቅት ምክንያት በማድረግ በመካሄድ ላይ ያለው ጦርነት ለጊዜው እንዲገታ ውሳኔ ማስተላለፉት ሲገለጥ፣ የየመን አየር ኃይል በሰነዘረው ጥቃት ሳቢያ ሰማንያ ንፁሓን የክልሉ ነዋሪ ዜጎች ለሞት ዳርገዋል የሚባለው ጉዳይ የሚያጣራ አንድ ድርገት መመልመሉ በይፋ አስታውቀዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.