2009-09-21 13:20:04

ዓለም ዓቀፍ የአቶሚክ ኃይል ምንጭ ተቆጣጣሪ ድርጅት


እ.ኤ.አ. ከመስከረም 15 ቀን እስከ መስከረም 18 ቀን 2009 ዓ.ም. ዓለም አቀፍ የአቶሚክ ኃይል ምንጭ ተቆጣጣሪ ድርጅት 53ኛው ዓለም አቀፋዊ ስብሰባውን እንዳካሄደ ተገልጠዋል። በዚህ በተካሄደው ስብሰባ የቅድስት መንበር RealAudioMP3 ልኡካንን መርተው የተሳተፉት እና ንግግር ያሰሙት ብፁዕ ኣቡነ ማርቸሎ ሳንቸስ ሶሮንዶ መሆናቸው ሲገለጥ፣ ብፁዕነታቸው የጦር መሣሪያ ትጥቅ መፍታት እና ማምከን እንዲሁም ጸረ ሰው ረፍራፊው የጦር መሣሪያ ጨርሶ እንዲወገድ፣ የአቶሚክ ኃይል ምንጭ ከፍ እያለ በመሄድ ላይ ያለው የተጠቃሚነት ጥያቄ፣ አሸባሪነት፣ ሕገ ወጥ የኑክሊያር ንግድ የመሳሰሉት ርእሶች በማስደገፍ በተካሄደው ውይይት ተገኝተው ባሰሙት ንግግር ነጻና ሰብአዊነት የተካነው የአብሮ የመኖር ጉዳይ እንዲረጋገጥ ከተፈለገ ረፍራፊው ጸረ ሰው የጦር መሣሪያ ትጥቅ መፍታት እና ብሎም ማምከን እጅግ አስፈላጊ እና ወሳኝ ነው ካሉ በኋላ፣ የቅዱስ አብታችን ር.ሊ.ጳ በነዲክቶስ 16ኛ ፍቅር በሓቅ የተሰኘውቸውን አዋዲት መልእክት በመጥቀስ፣ ምርምር እና ተግባር በማቆራኘት ሰላማዊ የአብሮ የመኖር ጥሪ እንዲረጋገጥ ዘወትር ካለ መሰላቸት እውነተኛው ኵላዊው የሰብአዊ እድገት ማነቃቃት አስፈላጊ መሆኑ አብራርተዋል።

የአቶሚክ ኃይል ምንጭ ሰውን እና ተፈጥሮን ለሚጎዳ ተግባር ሳይሆን ሰላም ለመገንባት እና ለእውነተኛው እድገት አገግሎት ይውል ዘንድ ብፁዕ ኣቡነ ሶሮንዶ በማሳሰብ፣ የሰውን ልጅ ማእከል ያደረገ የጋራው ጥቅም ያነጣጠረ እንጂ ወታደራዊ እና ኤኮኖሚያዊው ብሔራዊ አቀፍ ኃይል ለማጉላት መዋል የለበትም ብለዋል። በመጨረሻም ብፁዕነታቸው ቅድስት መንበር የኑክሊየር ጦር መሣሪያ ጨርሶ እዲወገድ የሚለው እቅድ የሰላም እና የደህንነት ጉዳይ ለሚመለከት ተግባር እና ውይይት ማእከል መሆኑ እንደሚገባው ካለ መታከት እንደምታሳስብ በመጥቀስ የዓለም አቅፍ ማኅበርሰብ የኑክሊያር ጦር መሣሪያ እንዲወገድ የአለም አቀፍ ስምምነት ሙሉ በሙሉ እንዲረጋገጥ ተጨባጭ ግልጽ እና አስተማማኝ ውሳኔዎች እውን ማድረግ ይጠበቅበታል ብለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.