2009-09-21 13:25:59

ኬንያ፣ በድርቅ እና በርሃብ ለተጎዳው ሕዝብ ድጋፍ


የኬንያው ሕዝብ በዝናብ እጥረት ሳቢያ በተከሰተው ድርቅ እርሃብ እና የውሃ መጠጥ ችግር በጠና መጠቃቱ ሲገለጥ፣ ዓለም አቀፍ የካቶሊክ ተራድኦ ማኅበር ከኬንያ ካቶሊክ ቤተ ክርስትያን ጋር በመተባበር በእርሃብ እና በመጠጥ RealAudioMP3 ውኃ እጥረት ለሚሰቃየው ህዝብ አስፈላጊው እርዳታ እያቀረበ መሆኑ ቺዛል ኔውስ የዜና አገልግሎት አስታውቀዋል።

በአገሪቱ የሚታየው ድርቅ በመተመጣጠነ የምግብ እጥረት የሚሰቃዩት ሕጻናት ብዛት እጅግ ከፍ እንዲል ማድረጉ እና የተከሰተው የምግብ እጥረት ለመጋፈጥ ህዝቡ በቀን አንዴ እንደሚመገብ እና ይኽ ዓይነቱ አመጋገብ የጤና መታወክ አደጋ እያስከተለ ሲሆን፣ የአገሪቱ መንግሥት የሰጠው መገልጫ 10 ሚሊዮን የኬንያ ህዝብ ለምግብ እጥረት አደጋ መጋለጡ ሲያመለክት፣ ዓለም አቀፍ የካቶሊክ የእርዳታ ድርጅት ይኸንን ሁሉ እግምት ውስጥ በማስገባት ከኬንያ ቤተ ክርስትያን ጋር በመተባበር አስፈላጊው እርዳታ በማቅረብ መርሃ ግብር አቢይ አገልግሎት እየሰጠ መሆኑ የዜናው አገልግሎት አስታውቀዋል።

ይህ ዓለም አቀፍ የካቶሊክ ተራድኦ ማኅበር አስፈላጊ እርዳታ በማቅረብ ረገድ ብቻ ሳይሆን የውኃ አጠቃቀም ሕንጸት በማቅረብም አቢይ የድጋፍ ሚና እየተጫወተ መሆኑ ቺዛል የዜና አገልግሎት አስታወቀ።








All the contents on this site are copyrighted ©.