2009-09-21 13:15:02

እውነተኛው ጥበብ

 


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ትናንትና እሁድ እኩለ ቀን ከካስተልጋንደልፎ ሓዋርያዊ አዳራሽ መስኮት የመልአከ እግዚአብሔር ጸሎተ ሥርዓት ከመምራታችው በፊት “በእግዚአብሔር ጥበብ መሳተፍ ይቻላችሁ ዘንድ RealAudioMP3 ሓሰት እና ራስ ወዳድነትን አሸንፉ ሓቅን ውደዱ በቀልና ጥላቻን ተዉ” ሲሉ ኣሳስበዋል።

ቅዱስነታቸው በቅርቡ በአፍጋኒስታን በጣሊያን ወታደሮች ላይ የወረደው የመግደል አደጋ ከልብ እንዳሳዘናቸው ገልጠው ሰላም እንዲሰፍን ተማጥነዋል።

በሚቀጥለው ሳምንት ወደ ቸክ ረፓብሊክ ሓዋርያዊ ጉብኝት እንደሚያደርጉ አስታውሰውም ኤውሮጳ እንደገና የእምነት እና የተስፋ ትርጉም የማጤን ግዴታ እንዳለባት አረጋገጠዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.