2009-09-19 15:56:46

በአፍጋኒስታን ስድስት የጣልያን ወታደሮች እና አስር ሲቪሎች ተገደሉ፡


በአፍጋኒስታን ካቡል ላይ በመኪና የተጠመደ ኃይለኛ ቦምብ ፈንድቶ ስድስት የጣልያን ወታደሮች ገድሎ አስር ሲቪሎች ማቁሰሉ ተገልጸዋል።

ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ አሳዛኝ ድርጊቱ እንደተረዱ የተሰማቸውን ጥልቅ ሐዘን ገልጠው በዚሁ ጥቃት ሕይወታቸው ላጡ ወታደሮች እንደሚጸልዩ እና ከቤተሰቦቻቸው አጠገብ መሆናች እና እግዚአብሔር ጥናቱ እንዲሰጣቸው እንደተመኙላቸው የቅድስት መንበር ቃል አቀባይ አባ ፈደሪኮ ሎምባርዲ ለጋዜጠኞች ገልጠዋል።

ጣሊባን የተባለ የአፍጋኒስታን አክራርሪ ቡድን የግድያ ድርጊቱ ባሌበት መሆኑ መግለጫ ማውጣቱ ከካቡል የደረሰ ዜና አመልክተዋል ።

ይህ ሁሉ የፈሰሰ ደም በመጨረሻ በሰላም ይተካ ዘንድ የቅድስት መንበር ቃል አቀባይ አባ ፈደሪኮ ሎምባርዲ ያላቸውን ተስፋ ገልጠዋል ።

የጣልያን ረኪበ ጳጳሳት ሊቀ መንበር የጀኖቫ ከተማ ሊቀጳጳሳት ብፁዕ ካርዲናል አንጀሎ ባኛስኮም በጣልያን ጳጳሳት እና ቤተክርስትያን ስም የተሰማቸውን መራራ ሐዘን ገልጠዋል።

በዚሁ ትናንትና ካቡል ላይ በጣሊባኖች የተወሰደው የማጥቃት ርምጃ በሳላሳ ሰላማውያን ሰዎች ከባድ እና ቀላል መቁሰልት ማድረሱ የአፍጋኒስታን የመከላከያ ሚኒስቴር አስታውቀዋል።

ከ2004 እኤአ እስከ ዛሬ ድረስ አፋጋኒስታን ላይ የተገደሉ የጣልያን ወታደሮች ሃያ አንድ መድረሱ የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አመልክተዋል።

የጣልያን መንግስት ርእሰ ብሔር ጠቅላይ ሚኒስትር የሀገሪቱ የሕግ መወሰኛ እና መምርያ ምክር ቤቶች ፕረሲዳንቶች አፍጋኒስታን ላይ የስድስት ወታደሮች ሕይወት ጥፋት እጅግ እንዳሳዘናቸው ይፋዊ መግለጫ የሰጡ ሲሆን ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዚሁ አስከፊ የግድያ ተግባር የጣልያን ወታደሮች በአፍጋኒስታን የሚያደርጉት የሰላም ተልእኮ የማይደናቀፍ እና ቀጣይ መሆኑ ገልጸዋል።

በ2003 እኤአ አቆጣጠር አስራ ዘጠኝ የጣልያን ወታደሮች በዒራቅ ናሲሪያ ላይ በተመሳሳይ ሕይወታቸው እንዳጡ የሚታወስ ነው።

ሶስት ሺ ሶስት መቶ የጣልያን ወታደሮች ከሌሎች ሀገራት አቀፍ ሰራዊት በመተባበር አፍጋኒስታን ውስጥ በየሰላም ተልእኮ ተሰማርተው እንደሚገኙ ይታወሳል።








All the contents on this site are copyrighted ©.