2009-09-18 13:35:02

የቅዱስ አባታችን እና የብፁዕ ኣቡነ ሂላሪዮን ግኑኝነት

 


የሩሲያ ፓትሪያርክ የውጭ እና ከሌሎች አቢያተ ክርስትያናት ጋር የሚደረገውን ግኑኝነት የሚንክባከበው ጽ/ቤት ሊቀ መንበር ብፁዕ አቡነ ሂላሪዮን ዛሬ ጠዋት በካስተል ጋንደልፎ ከቅዱሱ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ ጋር RealAudioMP3 መገናኘታቸው የቅድስት መንበር መግልጫ ያመለክታል።

ብፁዕ አቡነ ሂላሪዮን ትላትና የክርስትያኖች አንድነት የሚያነቃቃው ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፁዕ ካርዲናል ቫልተር ካስፐር ጋር መገናኘታቸው ሲታወቅ፣ ግኑኝነት በተመለከተ ብፁዕ ካርዲናል ካስፐር ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ በካቶሊክ እና በሩሲያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስትያን መካከል ያለው ግኑኝነት አዲስ ገጽታውን ያጎላ እና ከዚህ በፊት የነበሩትን አለ መግባባት እና ውጥረት ያገለለ የተረጋጋ እና አወንታዊነቱን የመሰከረ ነው ብለዋል። በዚህ አጋጣሚም ብፁዕ አቡነ ሂላሪዮን ለቅዱስ አብታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ያላቸውን አድናቆት እና አክብሮት በይፋ መግለጣቸው ብፁዕ ካርዲናል ካስፐር አስታውቀው፣ በኢስቶኒያ ምክንያት በሞስካ እና በቁስጥንጥንያ መካከል ተከስቶ የነበረው ውጥረት ባሻገር ያተኮረ እና ውጥረቱን ያገለለ ሁኔታ መፈጠሩንም አውስተው፣ በእውነቱ የሞስካ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስትያን ለመተባበር እና ለመወያየት ያላትን አዲስ እርምጃ ያጎላ አጋጣሚ ነው ብለዋል።

የካቶሊክ እና የሞስካ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስትያን መካከል ያለውን ግኑኝነት ለማጠናከር የሚያግዝ የሆነውን ሁሉ ገቢራዊ ለማድረግ እና የሩሲያ ቤተ ክርስትያን በካቶሊክ ቤተ ክርስትያን ላይ የነበራት አሉታዊ ቅድመ ፍርድ እና በሃይማኖቶች መካከል ለአንድነት አልሞ የሚደረገውን ግኑኝነት ከወዲሁ በጥርጠራ የመመልከቱ አዝማሚያ ማግለልዋ ያረጋገጠ ግኑኝነት ነበር ብለዋል።

በቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ፓ. በነዲክቶስ እና በፓትሪያርክ ብፁዕ ወቅዱስ ኪሪሊ መካከል ግኑኝነት ይደረግ ዘንድ የሁሉም ፍላጎት ቢሆንም ቅሉ፣ የት እና መቼ እንደሚሆን በሚለው ርእሰ ጉዳይ ምንም ዓይነት ውይይት አለ መደረጉም ጠቅሰው የሁለቱ የሃይማኖት መሪዎች ገና ሜትሮፖሊ እያሉ መገናኘታቸው በማስታወስ፣ በመሪነት ደረጃ ግኑኝነቱ አስፈላጊ ቢሆንም፣ ሁለቱ አቢያተ ክርስትያን በተለያዩ ጽሕፈት ቤቶቻቸው አማካኝነት ግኑኝነት ከማድረግ አልተቆጠቡም በማለት የሰጡትን ቃለ ምልልስ ደምድመዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.