2009-09-18 13:42:53

ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ እ.ኤ.አ. 2011 ዓ.ም. የሚካሄደው ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን በስፐይን ርእሰ ከተማ እንዲካሄድ ውሳኔ ከሰጡበት እለት ጀምሮ ይኽው በማድሪድ የተለያዩ ቅድመ ዝግጅቶች እየተከናወነ RealAudioMP3 መሆኑ የማድሪድ ሊቀ ጳጳሳት ካርዲናል አንቶኒዮ ማሪያ ርውኮ ቫረላ መግለጣቸው ዜኒት የዜና አገልጎት አስታወቀ።

ከባለፈው ሰኞ ጀምሮ የዚህ ሁሌ በያመቱ በካቶሊክ ቤተ ክርስትያን አነሻሽነት ለሚካሄደው ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን አርማ የሆነው ትልቁ መስቀል በስፐይን በሚገኙት ሰበካዎች ኡደት እያደረገ መሆኑ ሲታወቅ፣ በዚህ እ.ኤ.አ. ከነሓሴ 15 ቀን እስከ ነሓሴ 21 ቀን 2011 ዓ.ም. የሚካሄደው የዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ መሪ ትምህርት በመስጠት እንደሚሳተፉ እና የማጠቃለያው መሥዋዕተ ቅዳሴ እንደሚያሳርጉም ከወዲሁ ሲታወቅ፣ ነሐሴ 18 ቀን 2011 ዓ.ም. በካታላና ዋና መንገድ የፍኖተ መስቀል ጸሎተ ሥርዓት እንደሚካሄድም ተገልጠዋል።

ለዚህ የማድሪዱ የዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን ይፋዊ ድረ ገጽ የበአሉ ዋና አዘጋጅ ኮሚቴ በይፋ ያሳወቀ ሲሆን፣ በዚህ ዓቢይ የወጣቶች በዓል ለሚሳተፉት ወጣቶች የስፐይን ካቶሊክ ቤተ ክርስትያን ቁምስናዎች ገዳማት እና እንዲሁም መንግሥት መስተንግዶ እንደሚያደርግ ኮሚቴው በማረጋገጥ፣ በዚህ ካንድ ሚሊዮን በላይ የሚገመቱ ወጣቶች ይሳተፉበታል ተብሎ በሚጠበቀው አቢይ በዓል 15.000 የበጎ እድራጎት አባላት አስፈላጊው ትብብር በማቅረብ እንደሚሰማሩም ከወዲሁ ተገልጠዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.