2009-09-18 13:40:35

ኩባ፣ በወህኒ ቤቶች መሥዋዕተ ቅዳሴ ለማቅረብ መፈቀዱ


በኩባ ወህኒ ቤቶች መንፈሳዊ አገልግሎት እለፎ አልፎ ይሰጥ የነበረ ቢሆንም ቅሉ እስረኞች የመሥዋዕተ ቅዳሴ ሥርዓት የማግኘቱ ፍላጎት ለሃምሳ ዓመት ሳይከበር ቆይቶ ይኸው ለመጀመሪያ ጊዜ የኩባ ርእሰ ብሔር ራውል ካስትሮ RealAudioMP3 የፈቃድ ውሳኔ ማስተላለፋቸው ሲገለጥ፣ ውሳኔው ለኩባ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት እጅግ ደስ አሰኝተዋል።

አባ ኾሴ ፈሊክስ ፐረዝ ይህ ፍቃድ እንዲረጋገጥ የኩባ ካቶሊክ ቤተ ክርስትያን ለመንግሥት ጥያቄ ስታቀርብ እና ስለ ጉዳዩ ስተወያዩ ቆይታ፣ ይኸው አሁን ጥያቄው አወንታዊ ምላሽ ማገኘቱ እጅግ የሚያረካ ብቻ ሳይሆን፣ እግዚአብሔርንም ለማመስገን አቢይ ምክንያትም ነው ብለዋል። በኩባ የተሰበሰበው የወንጌላውያን አቢያተ ክርስትያን ምክር ቤት ጉባኤ ጭምር ተመሳሳይ መግለጫ ማስተላለፉ ተረጋግጠዋል። እስረስኞች በሚያቀርቡት ጥያቄ መሠረት የኩባ ካቶሊክ ቤተ ክርስትይያ ካህናት ልዩ ፍቃድ በመጠየቅ ለእስረኞች መንፈሳዊ እንክብካቤ ያቀርቡ እንደነበር የሚታወቅ ሲሆን፣ ነገር ግን በወህኒ ቤቶች ያምልኮ ሥርዓት ለመፈጸም ፍቃድ ሲሰጥ ግን ይህ የርእሰ ብሄር ራውል ክስትሮ ውሳኔ ከሃምሳ ዓመት ወዲህ የተገኘ የመጀመሪያ መሆኑ አባ ኾሴ ፈሊክስ ፐረዝ አስታውሰዋል።

ር.ሊ.ጳ. የእግዚአብሔር አገልጋይ ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ እ.ኤ.አ. በ 1998 ዓ.ም. ኩባን እንደጎበኙና ይህ ጉብኝት በዚህች አገር በዓለ ልደት በይፋ ብሔራዊ በዓል ሆኖ ይከበር ዘንድ ፈቃድ እንዲሰጥ ማድረጉ የኩባ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ዋና ጸሓፊ ኣባ ኾሴ ፈሊክስ ፐረዝ አስታውሰው፣ ስለዚህ በወህኒ ቤቶች በልደት በዓል ብቻ ዘወትር መሥዋዕተ ቅዳሴ ለማቅረብ የሚፈቅድ ውሳኔ ነው ብለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.