2009-09-18 13:32:56

ብፁዕ ካርዲና በርቶኔ የሮማኒያ መራሔ መንግሥት ተቀብለው አነጋገሩ


ትላንትና ጧት የቅድስት መንበር ዋና ጸሓፊ ብፁዕ ካርዲናል ታርቺዚዮ በርቶኔ በቅድስት መንበር የውጭ ጉኑኝነት ጉዳይ ዋና ጸሓፊ ብፁዕ አቡነ ዶሚንክ ማምበርት ተሸኝተው ከትላትና በስትያ ከርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት RealAudioMP3 ጋር በመግገናኘት በሮማኒያ እና ቅድስት መንበር ጋር ስላለው ግኑኝነት እንዲሁም አንገብጋቢ ኤውሮጳዊው እና ዓለም አቀፍዊው ነክ ጉዳይ ርእሰ በማድረግ ከተወያዩት የሮማኒያ መራሔ መንግሥት ኤሚል ቦክን ተቀብለው ማነጋገራቸው የቅድስት መንበር መግለጫ ያመለክታል።

ብፁዕ ካርዲናል በርቶኔ በግኑኝነቱ ወቅት በቡካሬስት የሚገኘው የቅዱስ ዮሴፍ ካቴድራል ጉዳይ በተመለከተ እርሱም ካቴድራሉ አጠገብ ሊገነባ ታቅዶ ያለው አቢይ ሰማይ ጠቀስ ፎቅ የካቴድራሉ መሠረት ላደጋ የሚያጋልጥ መሆኑ የሮማኒያ የብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ያሰሙት ቅሬታ ማእከል በማድረግ መወያየታቸው ከቅድስት መንበር የተሰራጨው ዜና ይጠቁማል።








All the contents on this site are copyrighted ©.