2009-09-17 09:46:01

የብፁዕ ካርዲናል ሳንድሪ ፖላንድ ጉብኝት.


በቅድስት መንበር የምስራቃዊት ቤተክርስትያን ማኅበር ብፁዕ ካርድናል ለኦናርዶ ሳንድሪ ፖላንድን በመጐብኘት ላይ መሆናቸው የቫቲካን መግለጫ አስታውቀዋል።

ብፁዕ ካርዲናል ሳንድሪ ፖላንድ እንደገቡ እንደገለጹት ፡ ጉብኝቱ የላቲን ሥርዓት እና ግሪክ ካቶሊካዊት ቤተክርስትያን ሕይወት ለማወቅ እና ከአብያተ ክርስትያናቱ ተጠሪዎች ጋር ሐሳብ ለሐሳብ መለዋወጥ በእጅጉ ይጠቅማል ።

ብፁዕ ካርዲናል ለኦናርዶ ሳንድሪ በፖላንድ የሳንዶምየርጽ ሀገረ ሰብከት ጳጳስ ብብጹዕ ኣአቡነ ኒትኪቪጽ በተደረገላቸው ጥሪ መሠረት ሀገረ ስብከትመጐብኘታቸው ተመልክተዋል።

ብፁዕ አቡነ ኒትኪቪጽ በቫቲካን የምስራቃዊት ቤተክርስትያን ምክትል ሐላፊ የነበሩ ናቸው። ብፁዕ ካርዲናል ለኦናርዶ ሳንድሪ በፖላንድ ከየቅድስት መንበር ሐዋርያዊ ውኪል ከብፁዕ አቡነ ኮቫልሲስኪ ከየግሪክ ካቶሊካዊት ቤተክርስትያን ዋና ሐላፊ ከሜትሮፖሊታን ሚካሊክ ጋር መገናኘታቸው አብሮ የደረሰ ዜና አስገንዝበዋል።

ከዚህ ባሻገር ብፁዕ ካርዲናል ሳንድሪ ከፖላንድ ጳጳሳት ጋር በጋራ በግሪክ ካቶሊካዊት ቤተክርስትያን መስዋዕተ ቅዳሴ ማሳረጋቸው ተገልጸዋል።

ብፅዕነታቸው በዚሁ መስዋዕተ ቅዳሴ ለተገኙ ጳጳሳት እና ምእመናን የቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ ሐዋርያዊ ቡራኬ እና አባታዊ ሰላምታ ማድረሳቸውም ተያይዞ ተነግረዋል።

ብፁዕ ካርዲናል ሳንድሪ በፖላንድ የመለኮታዊ ምሕረት ቤተክርስትያን ባርከው ቀድሰው እና መርቀው የከፈቱ ሲሆን የምእመናን መንፈሳውነት እንደማረካቸው በሄዱበት ቦታ በእምነታቸው ጽኑ ምእመናን መታዘባቸው አመልክተው ፖላንድን ለመጐብኘት መቻላቸው እግዝአብሔርን አምሰግናለሁ ማለታቸው ተዘግበዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.