2009-09-17 09:27:33

የቅዱስ አባታችን ቅርበት እና የማበረታታቻ መልእክት ለምእመናን


ጳጳሳዊ የምስራቅ አቢያተ ክርስትያን የሚንከባከበው ቅዱስ ማኅበር ኅየንተ ብፁዕ ካርዲናል ለዮናርሶ ሳንድሪ በፖላንድ የግሪክ ሥርዓት የምትከተለው የካቶሊክ ቤተ ክርስትያን በቅርቡ መጎብኘታቸው የሚዘከር ሲሆን፣ RealAudioMP3 ይህ ሓዋርያዊው ጉብኝት የላቲን ሥርዓት የምትከተለው የካቶሊክ ቤተ ክርስትያን እና የግሪክ ሥርዓት የምትከተለው የካቶሊክ ቤተ ክርስትያን ሕይወት እና ተጨባጩ ወቅታዊው ሁኔታ እውቅናን የሰጠ መሆኑም ተገለጠ።

ብፁዕ ካርዲናል ሳንድሪ የሳንዶማይርዝ ሰበካ ሊቀ ጳጳሳት የዚህ የምስራቅ አቢያተ ክርስትያን የሚንከባከበው ቅዱስ ማኅበር ዋና ጸሓፊ ብፁዕ አቡነ ክርዝይስቶፍ ኒትካይዊች ባደረጉላቸው ጥሪ መሠረት ይኸንን ሰበካ ለየት ባለ መልኩ የጎበኙ ሲሆን፣ የብፁዕ አቡነ ኒትካዊች የስታሎዋ ዎላ ተባባሪ ካቴድራል ሓዋርያዊ መሪነት ኃላፊነት በይፋ በሚገልጠው ሥነ ሥርዓት ተሳትፈው በኦስትሮዋይች ከተማ በፖላንድ ከቅድስት መንበር ሓዋርያዊ ወኪል ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ ኣቡነ ጆሰፍ ኮዋልችዝይክ እና በፖላንድ ከግሪክ ሥርዓት ከምትከተለው የካቶሊክ ቤተ ክርስትያን መሪ ከፕርዘምይስል ና ቫርሳቪያ ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ አቡነ ጃን ሚካሊክ ጋር ተገናኝተው ሰፊ ውይይት ማካሄዳቸው ከቅድስት መንበር የተሰራጨ መግለጫ ያመለክታል።

ስለ ሓዋርያዊው ጉብኝት በማስመልከት ብፁዕ ካርዲናል ሳንድሪ ከቫቲካን ሬዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ የፖላንድ የግሪክ ሥርዓት የምትከተለው የካቶሊክ ቤተ ክርስትያን በመጎብኝት የቤተ ክርስትያንዋ ወቅታዊው ሁኔታ ቀርበው በመመልከት እና ከዚህች ቤተ ክርስትያን ሓዋርያው መሪዎች እና ውሉደ ክህነት እንዲሁም ምእመናን ጋር ተገናኝተው የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ቅርበት እና የማበረታታቻ መልእክት ማስተላለፋቸው ገልጠው በተመሳሳይ መልኩም ህዝቡ እና ቤተ ክርስትያንዋ እንዲሁም ጳጳሳት እና ካህናት እንዲሁም ምእመናን ለቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ያላቸውን ፍቅር እና አክብሮት ቀርበው ለማረጋገጥ መቻላቸው አስታውቀዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.