2009-09-17 09:29:37

ውሁድ ልብ ያነቃቃው ሱባኤ በታይዋን


በታይዋን ውሁድ ልብ ጳጳሳዊ ምክር ቤት ያነቃቃው ሱባኤ እ.ኤ.አ. ከ መስከረም 6 ቀን እስከ መስከረም 11 ቀን 2009 መካሄዱ ሲታወቅ፣ ቅዱስ አብታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ሱባኤው በተካሄደበት ወቅት RealAudioMP3 ባስተላለፉት ምልእክት መንፈሳዊ ሲባኤ በተለያየ ዘርፍ ተሰማርተው አገልግሎት ለሚሰጡት እና ለሚሰቃዩት የግብረ ሰናይ አገልግሎ ለሚደርሳቸው ሁሉ የመተሳሰብ እና የመደጋገፍ እሰይታ ዳግም በውስጣቸው ኅያው የሚያደርግ ጸጋ ነው እንዳሉ የሚዘከር ነው። በዚህ በታይፒ ከተማ በሚገኘው በፉ ጄን የካቶሊክ መንበረ ጥበብ በተካሄደው መንፈሳዊ ሲባኤ በእስያ ክልል አገሮች በተለያዩ የቤተ ክርስያን የግብረ ሰናይ ማኅበራት እቅድ ተሰማርተው አገልግሎት የሚሰጡት እና የግብረ ሰናይ ማኅበራት የሚምሩት ከ26 አገሮች ከ 260 ሰበካዎች የተወጣጡ 6 ብፁዓን ካርዲናላት 60 ብፁዓን ጳጳሳት መሳተፋቸው ታውቀዋል።

የሱባኤው መንፈሳዊ መርኅ ቃል በማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ 25 ከቁጥር 31 እስከ 46 ያለው በተለይ ደግሞ “ያደረጋችሁት ሁሉ ለእኔ እንዳደረጋችሁት ነው” በሚለው የኢየሱስ ክርስቶስ ጥልቅ ቃል ላይ ይተመረኮዘ እንደነበርም ሲገለጥ፣ ሱባኤው ይኸንን ወንጌላዊ ጥሪ ፍቅር በሐቅ የተሰየመቸው በቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16 የተደረሰቸው አዋዲት መልእክት ጋር በማዛመድ ሰፊ አስተንትኖ እና ጥልቅ የሀሳብ ልውውጥ መካሄዱም ኤሺያን ኔውስ የዜና አገልግሎት አስታወቀ። በዚህ ሱባኤ ለተሳትፉት ከታይዋን ርእሰ ብሔር ማ ዪንግ ጄኦው የእንኳን ደህና መጣችሁ እና የመልካም መንፈሳዊ ሱባኤ መግለጫ መልእክት መተላለፉትም የዜናው አገልግሎት ያረጋገጣል።

ይህ በዲህ እንዳለ የጳጳሳዊው ውሁደ ልብ ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፁዕ ካርዲናል ፓውል ጆሴፍ ኮርደስ በታይዋን ሞራኮት የተሰየመው ዝናብ ቅልቅል ኃይለኛው አውሎ ነፋስ ያጠቃቸው እና አቢይ የሰው እና የንብረት ጉዳት የደረሰባቸው ክልሎች መጎብኘታቸው እና ለተጎዳው ህዝብ የእግዚአብሔርን ማጽናናት እና ፍቅሩንም ጭምር በመመስከር ቤተ ክርስትያን ለብቻቸው እንደማትተዋቸው ማረጋገጣቸው ተገልጠዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.