2009-09-17 09:32:00

ትምህርት የማግኘት እድል የሁሉ ሰው ዘር መብት ነው


በአለማችን 75 ሚሊዮን ሕጻናት የትምህርት እድል የተነፈጋቸው መሆኑ፣ ትምህርት የሁሉም ሰው ዘር መብት ነው የተሰኘው ዓላማ ያነገበ ተረ ደስ ሆመስ የተሰኘው ማኅበር በመግለጥ ይህ ችግር ችላ ሊባል RealAudioMP3 የማይገባው በዓለማዊ ትሥሥር ሂደት መፍትሔ ማግኘት ያለበት ጉዳይ መሆኑ እ.ኤ.አ. ባለፈው መስከረም 8 ቀን 2009 ዓ.ም. ታስቦ የአዋለው ዓለም አቀፍ የጸረ መሃይምነት ዕለት ምክንያት በማድረግ ባስተላልፈው መግለጫ ያሳስባል።

የዚህ የ ተረ ደስ ሆመስ በኢጣሊያ ለሚገኘው ቅርንጫፍ የማስታወቅያ እና የግኑኝነት ጉዳይ ተጠሪ ፓውሎ ፈራራ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ ለመጪው እድል ብቻ ታስቦ ሳይሆን የወቅታዊው ሁኔታ ጭምር እግምት ውስጥ በማስገባት የወዲሁ እለታዊው ኑሮ እንዲሻሻል እና የመጪው ሕይወት የበለጠ እንዲሆን የሚደረገው ጥረት ትምህርት ለሁሉም ማዳረስ ከሚለው መርሃ ግብር መጀመር አለበት፣ ከዚህ ጋር ተያይዞም የሁሉም ሰው ዘር ዕለታዊ እንጀራ የማግኘት መብት ማረጋገጥ ወሳኝ ነው፣ በአለማችን ብዙ ሕጻናት በተለያዩ ምክንያቶች ከትምህርት ገበታ ተገለው ያለባቸውን ድኽነት እና የቤተሰቦቻቸው ችግር ከወዲሁ ተካፋይ በመሆን ቤተሰብ በሚያደርገው እለታዊ እንጀራ በመሻት እቅድ በመሰማራት ገና በጨቅላ እድሚያቸ ለሥራ ዓለም ተዳርገው የጨቅላነት እድሚያቸ ተነጥቀው ይገኛሉ፣ ካሉ በኋላ ችግሩ በስፋት በአፍሪካ የሚታይ ሲሆን፣ በዚህች ክፍለ አለም ያስተማሪዎች የትምህርት ቤቶች እጥረት የትምህርት ቤቶች ርቀት ጭምር ችግሩ እንዲባባስ ማድረጉ አብራርተዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.