2009-09-15 09:42:03

ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ ሞልታን እንደሚጐበኙ ተገልጸዋል፡


ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ ፊታችን ዓመት 2010 እኤአ የሞልታ ጳጳሳት እና የሀገሪቱ መንግሥት ባደረጉላቸው ጥሪ መሠረት ሀገሪቱ ላይ ሐዋርያዊ ጉብኝት እንደሚያካሄዱ የቫቲካን መግለጫ አስታውቀዋል።

ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሞልታ ላይ የሚያካሄዱት ጉብኝት ሶስተኛ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳዊ ጉብኝት መሆኑም መግለጫው አስታውሰዋል ።

ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ በ1990 እና 2001 ሞልታን መብኘታቸው መጐብኘታቸው የሚታወስ ነው።

ርእሰ ሊቃነ ጳጳስት ከጣልያን ውጭ የሚያካሄዱት ሐዋርያዊ ጉብኝት አዘጋጅ እና ዶ/ር አስተባባሪ አልበርቶ ጋዝባሪ ሐዋርያዊ ጉብንቱ ለማዘጋጀት ፊታችን ጥቅምት ወር ወደ ሞልታ እንደሚዘልቁም ተያይዞ ተም አልክተዋል።

በቅዱሳን ሐዋርያት ትረካ መሠረት ቅዱስ ጳውሎስ ሐዋርያ በ60 ዓመተ ምሕረት ወደ ሮማ ሲጓዝ በሞልታ ደሴት ባሕር የመስጠም አደጋ አጋጥሞታል።

ፊታችን ዓመት 2010 ሐዋርያ ጳውሎስ በተጠቀሰው ባሕር የመስጠም አደጋ ያገጠመበት1950ኛው ዓመት መሆኑ ነው።

ሐዋርያ ጳውሎስ ከሶስት ወራት በኃላም ከየሞልታ ደሴት ባሕር ደቡባዊ ጣልያን ሲሲሊ ለመግባት ሶስት ወራት እንደፈጀበትም ቅዱሳን የሐዋርያት ማስታወሻ እንደሚያመልክትይነገራል።

ይሁን እና ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ በ2005 እኤአ በቅድስት መንበር የሞልታ ደሴት አዲስ አምባሳደር ተቀብለው ባነጋገሩበት ግዜ ፡ ጥልቅ የሆነ የሞልታ ክርስትያናዊ ታሪክ እና እሴት አስታውሰው ፡ ቅድስት መንበር እና ሞልታ የትብብር እና ሰላም ግኑኝነት ለመምስረት እንደሚችሉ አውስተው ነበር።

በቅርቡ የሞልታ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ፓውል ክረሞና የሞልታ ደሴት ህዝብ ከ1950 ዓመተ ምሕረት በፊት ከቅዱስ ጳውሎስ ሐዋርያ እንደትባበረ ሁሉ አሁንም ከአፍሪቃ የሚፈልሱ ስደተኞች ተቀብሎ እንድያስተናግዳቸው አሳስበው ነበር ።

የሞልታ ህዝብ የውጭ ሰው የሆነው ሐዋርያ ጳውሎስ ተቀብለው አስተናገዱት በማለት በሐዋርያት የተነገረው የሞልታ የእንግዳ ተቀባይነት ባህል እና ታሪክ እንደሚያንጸባርቅ ብፁዕ አቡነፓውል ክረሞና አያይዘው መግለጸቻው የሚታወስ ነው።

በመዲተራንያ ባሕር ማእከል የምትገኘው ደሴት ሞልታ በ1964 ከታላቅዋ ብሪጣንያ ቅኝ ግዛት የተላቀቀች 410 ሺ ህዝብ የሚኖርባት ትንሽ ደሴት መሆንዋ ይታወቃል።

ህዝብዋ በመቶ ዘጠና ስምንት ካቶሊካዊ እምነት የሚከትል እና የኤውሮጳ ሕብረት አባል መሆንዋም አይዘነጋም።








All the contents on this site are copyrighted ©.