2009-09-14 15:49:48

እግዚአብሔር ለኛ ያለው ፍቅር አቢይ ኃላፊነት ነው


የኢጣሊያ የብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ሊቀ መንበር የጄኖቫ ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ ካርዲናል አንጀሎ ባኛስኮ ትላትና እሁድ በጀኖቫ የቅድስት ካተሪና ዘ ጆኖቫ 100ኛ ዓመት መታሰቢያ ያረገውን መሥዋዕተ ቅዳሴ RealAudioMP3 በመምራት ባሰሙት ስብከት፣ በእግዚአብሔር መፈቀራቸን እና ፍቅሩን ለመግለጥ አቢይ የቃል እና የተግባር ኃላፊነት አለብን ካሉ በኋላ ስለዚህ ያፈቀረን ፍቅር በማፍቀር መኖር እንዳለብን እና ያፈቀረን ፍቅር ኃላፊነትም ነው እንዳሉ ተገልጠዋል።

ያፈቀረን እና ለኛ ካለው ፍቅር በመነሳት እኛን ከሞት ለማዳን ሕይወቱን እስከ መስጠተ ያልሳሳው እግዚአብሔር የእምነታችን ማእከል ነው፣ ስለዚህ የዚህ ቀድሞ ያፈቀረን ፍቀር ያለብን ኃላፊነት ቀላል አይደለም፣ በርሱ እርዳታ ይኽ በነጻ የተቀበልነው ለሌሎች በማካፈል በሕይወታችን ልንመሰክረው ፍቅሩ ያስገድደናል፣ የእምነቷ ማእከል የእግዚአብሔር ፍቅር ያደረገች የቅድስት ካተሪና ዘ ጆኖቫ አብነትን እንከተል እንዳሉም ሲገለጥ፣ ይህች ቅድስት እ.ኤ.አ በ 1447 ዓ.ም. የመለኮታዊ ፍቅር ደናግል ማኅበር የመሠረተች በ 1510 ከዚህ ዓለም በሞት የተለየች በ 1737 ቅድስና ታውጆላትት በ 1943 ዓ.ም. የኢጣሊያ የሕክምና ቤት ተባባሪ ጠባቂ ቅዱስ ሆና መሰየሙ አቨኒረ የተሰየመው የኢጣሊያ የብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት እለታዊ ጋዜጣ ትላንትና ባወጣው ኅትመቱ ያመለክታል።








All the contents on this site are copyrighted ©.