2009-09-12 09:50:43

ፊታችን ጥቅምት ወር መጀመርያ ሳምንት ላይ ስለ ሚጀመረው የአፍሪቃ ጳጳሳት ሲኖዶስ ውይይት ተካሄደዋል.

 


ልዑካነ ቅዱስ ወንጌል እና ጋዜጠኞች በቅርቡ ስለሚካሄደው የአፍሪቃ ጳጳሳት ሲኖዶስ ትኩረት ሰጥተው ተወያይተዋል ።

ፊታችን ጥቅምት ወር ከአራት እስከ ሃያ አምስት ቀን ባለው ግዜ እዚህ ቫቲካን ውስጥ የአፍሪቃ ጳጳሳት ሲኖዶስ እንደሚከናውን የሚታወስ ነው ።

አፍሪቃውያን ጳጳሳት ዕርቅ ፍትሕና እና ሰላም በአፍሪቃ ትኩረት ሰጥተው ጥልቅ እና ሰፊ ውይይት ለማካሄድ እቅድ እንዳላቸው ከወዲሁ መገለጡም የሚታወስ ነው ።

የቅዱስ ወንጌል ልዑካን ባለ በጎ ፈቃድ ሰዎች ካቶሊካውያን ጋዜጠኞች የሲኖዶሱ ይዘታ እና የአፍሪቃ ክፍለ ዓለም ሁኔታ በተመለከት ሰፊ ውይይት ማካሄዳቸው ተመልክተዋል።

በዚሁ በካቶሊካዊ ተግባር አዳራሽ የተካሄደ ስብሰባ ከአስራ አምስት ዓመታት በፊት ቫቲካን ውስጥ የመጀመርያ የአፍሪቃ ጳጳሳት ሲኖዶስ ከተካሄደበት ግዜ እስካሁን ድረስ የአፍሪቃ አጠቃላይ ሁኔታ መገመገሙ ከአዳራሹ የወጥ መግለጫ አስታውቀዋል።

የካምቦኒ ማኅበር አባል የኒግሪጽያ ጋዜጣ ዳይረክተር እና ግማሽ ሕይወታቸው በአፍሪቃ ሀገራት ያሰለፉት አባ አለክስ ዛኖተሊ የአፍሪቃ ሁኔታ ትኩረት ሰጥተው ሲናገሩ ፡ አፍሪቃ ባለፉት አስራ አምስት ዓመታት በፊት አዎንታዊ እና አሉታዊ ለውጦች ስታካሂድ ትታያለች ያሉት ለብዙ ዓመታት በኬንያ ሞዛምቢክ እና ኡጋንዳ የኖሩ አባ አለክስ ዛኖተሊ፡ የዓለም ባንክ 280 ሚልዮን አፍሪቃውያን በቀን ሰባ አምስት ሳንቲም ያገኛሉ በማለት ይፋ ያደረገው መግለጫ ዋቢ በማድረግ ክፍለ ዓለሚቱ ህዝብዋ በርሐብ ከመሰቃየት አልተገላገለም ብለዋል።

አፍሪቃ ውስጥ የሚገኙ ሚስዮናውያን ማለት ልዑካነ ቅዱስ ወንጌል ከህዝቡ ጋር በመተባበር ማኅበራዊ ችግሮች ለመቅረፍ አበክረው እንደሚሰሩ ያመለከቱ አባ አለክስ ዛኖተሊ፡ በርዋንዳ እና ብሩንዲ የተካሄዱ ጨኻኝ ግጭቶች አሳዛኝ መኖራቸው እና ልዑካኑ ግጭቶቹ ለመግታት ዓቅም ስለ በማጣችን በእጅጉ ሐዘን ይሰማናል።

የአፍሪቃ ህዝቦች ክፍለ ዓለሚቱ ውስጥ የሚካሄዱ ግጭቶች እንዲገቱ ፍትህ እና ሰላም እንዲገኝ እንደሚመኙ የአህጉሪቱ መንግስታት ከየውጭ እና የውስጥ ከበርቴዎች በመተባበር

የህዝቡ ፍላጎት ወደ ጐን ትተው የራሳቸው ጥቅም ሲያፈላልጉ እንደሚታዩ በጥናት የተደገፈ ሪፖርት ለስብሰባው መቅረቡም ተዘግበዋል።

በቅርቡ የሚካሄደው የአፍሪቃ ጳጳሳት ሲኖዶስ የአፍሪቃ ህዝቦች የሚጠይቁት ፍትህ ሰለም እና ትብብር ገቢራዊ የሚሆንበት ሁኔታ እንደሚያፈላልጉም ተያይዞ ተገልጸዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.