2009-09-11 13:22:48

የተባበሩት የአሜሪካ መንግሥታት የጤና ጥበቃ መመሪያ ኅዳሴ


ርእሰ ብሔር ባራክ ኦባማ ባለፉት ቀናት ባገራቸው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ፊት ተገኝተው ሊከተሉት እና እግብር ላይ ሊያውሉት የሚሹትን ያገሪቱ የጤና ጥበቃ አዲስ መመሪያ በማስደገፍ ሰፊ ማብራሪያ RealAudioMP3 እና መግልጫ እንደሰጡበት ተገልጠዋል።

ርእሰ ብሔር ኦባማ ባሰሙት ንግግር፣ የመወቃቀስ የመተቻቸት ወቅት አክትሞለት ጊዜው የተግባር የትብብር እና የአዲስ ደንብ እና ሥርዓት ማረጋገጫ ወቅት ነው። ስለዚህ የጤና ጥበቃ ደንብ ካልታደሰ ያለው የኤኮኖሚ ቀውስ እየከበደ የኤኮኖሚ መዛባት፣ የብድር ጫና ከፍ እያለ የባንክ ቤቶች እና የሕዝቦች ኤኮኖሚ መቃወስ ከፍ እያደረገ እያንዳንዱ ዜጋ እራሱን ከተለያዩ ችግሮች ለማዳን ተስኖት ለተወሳሰበ ዘርፈ ብዙ ችግር እንደሚጋለጥ አያጠራጥርም ብለዋል። ይህ የባራክ ኦባማ የጤና ጥበቃ አዲሱ የመመሪያው ንድፍ እያንዳዱ የአሜሪካ ዜጋ የጤና ዋስትና ያለው የበለጠ የሌለው ደግሞ ተገቢ ሕክምና የማግኘት መብቱ እንዲጠበቅለት ሕክምና ማግኘት የሁሉም ዜጋ መብት መሆኑ የሚያምን እቅድ እንደሆነም ይነገራል።








All the contents on this site are copyrighted ©.